ኢትዮጵያ ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ704.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ችላለች

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ጥር 1 /2018 ዓ.ም

ባለፉት ስድስት ወራት እንደ ሀገር በተከናወነ የተቀናጀ ሥራ ከ704 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል ።

የገቢዎች ሚንስቴር የ6 ወራት የገቢ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያ በስድስት ወራት መሰብሰብ የቻለችው ከ704.4 ቢሊዮን ብር የሚልቅ ገቢ ባለፉት ጊዜያት ለዓመታት ሲሰበሰብ ከነበረው ገቢ የሚተካከል ነው ።

መንግሥት የሀገር ኢኮኖሚ ዕድገትን የሚደግፉ በርካታ የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ለተገኘው ውጤት ቁልፍ መነሾ ነው።

አፈጻጸሙ በገቢዎች ሚኒስቴር በግማሽ ዓመቱ ለመሰብሰብ ከታቀደው 640 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ውስጥ 704 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 110 በመቶ ማሳካት የተቻለበት ነው ።

የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው ዓመት ስድስት ወራት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር የ63 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ሲሆን ስኬቱ ኢትዮጵያ የውስጥ አቅሟን በማጎልበት እያንሰራራች ለመሆኑ ሁነኛ ማሳያ ተድርጎ የሚወሰድ ነው ።

በግማሽ ዓመቱ ከሀገር ውስጥ ታክስ 362 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን ከውጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ ከ341 ነጠብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ተስብስቧል ። ይህም ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛውን የገቢ አፈጻጸም ያሳየችበት ሀገራዊ ስኬት ነው ።

ለተጨማሪ መረጃ
👇https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts