ኢትዮጵያ ታምርት/የኢንዱስትሪው አብዮት/

በግብርና ዘርፍ ያገኘናቸው ስኬቶች በኢንዱስትሪው ዘርፍም በመደገም ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገር በቀል አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አሳድጓል ንቅናቄው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በጥራትና በብዛት ለማምረት እንዲሁም የግብርና እና ማዕድን ምርቶች ላይ ዕሴት ጨምሮ ለገበያ ለማቅረብ አዲስ ምዕራፍም ከፍቷል።በተለይ በጎጆ ኢንዱስትሪ የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት እንቅስቃሴ አካል የሆነው የገቢ ምርቶችን የመተካት ጅምር ጥረት እጅግ ተስፋ የሚሰጥ እንዲሁም በሁሉም የኢትዮጵያ ከባቢዎች መስፋት ያለበት ነው:: እያሳደግናቸው ያሉ አቅሞች ብልፅግናን ለማረጋገጥ እየረዱን ለሀገራችን ሆነ ለአህጉራችን ተስፋ እየሆኑ ይገኛሉ።

በስኬቶቻችን ላይ በመመስረት እና በሰፊ የሰው ኃይላችን በመደገፍ በሁሉም ዘርፎች እና መስኮች እድገታችንን ማፋጠን ይኖርብናል።

Similar Posts