ኢትዮጵያ አሁን ዕዳ ለመክፈል ምንም ዓይነት ችግር የለባትም !!!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ታላቋ አፍሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪኳን በራሷ ብዕርና ድምፅ ለመጻፍ የገበየችበትን የፓን-አፍሪካ የሚዲያ ሽልማት (AMA) ለማስተናገድ የተመረጠችው አፍሪካዊት መዲናችን አዲስ አበባ፣ የላቀ ሃላፊነቷን በብቃት እየተወጣች ትገኛለች። በመላ አፍሪካ ርዕሰ ከተሞች መካከል፣ ለዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲና የጋራ አህጉራዊ ተቋማት ማዕከል በሆነችው ምድራችን፣ ይህን ታላቅ የሚዲያ መድረክ ማስተናገድ ታላቅ ኩራት ነው። የአፍሪካ ሕብረት መናኸሪያ፣ የዲፕሎማሲና የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል…
ኢትዮጵያውያን ዳግም ለትውልድ የሚሻገር ታሪክ ለምንሰራበት ቀን እንኳን አደረሰን! #GreenLegacy ኢትዮጵያዊያን ማቀድ፤ መተግበርና፤ በትጋት ሰርቶ መፈፀም ብቻ ሳይሆን የጀመርነውን ማስቀጠል እንደምንችል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተግባር አሳይተናል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ገለፁ፡፡ ሚኒስተር ዴኤታዋ ዛሬ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃግብር መጀመርን አስመልክቶ አዲስ አበባ ከሚገኘው የሁኔታ መከታተያ ማዕከል መግለጫ…
ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ተግባር በሚገባበት ወቅት 20,000 ለሚሆኑ አርሶአደሮች ለሚያገለግል 9687.45 ሄክታር የእርሻ መሬት አስተማማኝ የመስኖ አቅርቦት ይኖረዋል። ይኽም የግብርና ምርታማነትን የሚያሳደግ፣ ለድርቅ የማይበገር ከባቢን የሚፈጥር ብሎም በማኅበረሰቡ አዳዲስ የሥራ እድል የሚፈጥር ይሆናል። ከነዚህ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ባሻገር የአካባቢውን የውሃ አስተዳደር ተቋማትን በማጠናከር፣ የአካባቢውን ሕዝብ ባለቤትነት በማሳደግ ብሎም የወልወልን ወንዝ ዘላቂ አጠቃቀም በማጎልበት የተሻለ የምግብ…
ሰላማዊ ካሳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሕብረ ብሄራዊነት የተከበረባት ጠንካራ አንድነት ያላት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ታላቁን ገዥ ትርክት በጋራ ልንገነባ ይገባል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊ ካሳ ተናገሩ፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ዛሬ በጀመሩት ውይይት ሚኒስትር ዴኤታዋ እንዳሉት እንደ መንግስት ኮሙኒኬሽን አመራርና ባለሙያ ለሃገራዊ ግንባታ አዎንታዊ ገዥ…
በሐረር ከተማ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የሐረሪ ክልል ባህል ማዕከልን የጋዜጠኞችና የኮሙኒኬሸን ባለሙያዎች ቡድን ዛሬ ጎብኝቷል፡፡ የባህል ማዕከሉ የወጣቶችን ስብዕና ለመገንባት እንዲሁም ስለ ሃገራቸውና ስለ ሃረሪ ክልል ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች ለማስተዋወቅ ያስችላል ተብሏል። ሐረር የመቻቻልና የፍቅር ከተማ መሆንዋን በተጨባጭ ለማሳየትና የቱሪዝም ማዕከልነቷን ለማሳደግ የባህል ማዕከሉ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የሐረሪ…