ኢትዮጵያ አዲስ የከተማ ልማት ምዕራፍ ውስጥ እየገባች ትገኛለች
በገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ትዕግሥት ፍስሀ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ አዲስ የከተማ ልማት ምዕራፍ ውስጥ እየገባች ሲሆን፥ ትኩረቱም ከተሞችን ማሰፋፋት ላይ ብቻ ሳይሆን ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንዲሁም ምቹ፣ ተወዳዳሪ፣ ሁሉን አቀፍና ዘመናዊ ከተሞች ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለጋራ ብልፅግና ቀጣይ ሞተር እንዲሆኑ ማድረግ ነው።


