ከሰባት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የነበረው የማክሮ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ስብራት ውስጥ የነበረ ነው።
የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት፣ የእዳ ጫና፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና የገበያ አለመረጋጋት ከለውጡ በፊት የነበሩ የማክሮ ኢኮኖሚው ዋና ስብራቶች ሆነው ቆይተዋል።
መንግሥት እነዚህን ስብራቶች ለመለወጥ በወሰዳቸው የለውጥ ተግባራት አሁን ላይ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ። ይህም ለውጥ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በፍጥነት እያደጉ ካሉ ሃገራት መካከል እንድትሆን አስችሏታል።
የመጀመሪያው እና ሁለተኛው የሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ጠንካራ እና አዳዲስ ተቋማት እንዲፈጠሩ አስችሏል። ለውጡ ካመጣቸው ውጤቶች መካከል የመንግስት ገቢን ለማሳደግ የሚያግዙ ጠንካራ፣ አዳዲስ እና ቀልጣፋ ስትራቴጂዎች እንዲነደፉ አድርጓል። ከለውጡ በኋላ የመንግስት ገቢ የውጭ ፍሰትን ጨምሮ በአምስት እጥፍ አድጓል።
የመንግስት የታክስ ገቢ በ400 % ጨምሯል ። የመንግስት ጠቅላላ ገቢ በ2010 ዓ.ም ከነበረበት ዛሬ ላይ 446 በመቶ ጨምሯል። ከውጭ ሃብት ፍሰትም ባለፉት ሰባት ዓመታት በአጠቃላይ 25 ቢሊየን ዶላር ማግኘት ያስቻለ ውጤት የተመዘገበበት ነው።በድህነት ተኮር ዘርፎች የዋለው በጀት በ2010 ከነበረበት በአራት እጥፍ ያደገ ነው። የበጀት ጉድለትን በተመለከተ በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 2.5 በመቶ በ2017 ወደ 0.9 በመቶ መቀነስ ተችሏል።
- አቶ አህመድ ሺዴ
የገንዘብ ሚኒስትር
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

