ከተሞች የነዋሪዎችን ፍላጎትና የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ ራሳቸውን በየጊዜው በመሰረተ ልማት ማሻሻልና ማዘመን ይኖርባቸዋል”
ሰላማዊት ካሳ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ
ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ መንግስት ማህበረሰቡ የሚያነሳቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች ለመስማት ከሚያደርገው ጥረት አንዱ ከመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ጋር የመስክ ምልከታ ማድረግ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሀዋሳ የመስክ ምልከታ እያረጉ ሲሆን በዚህ የመስክ ምልክታ ከተሞች የነዋሪዎችን ፍላጎትና የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች መመለስ እንዲችሉና የቱሪስት ቁጥርን ማስተናገድ በሚያስችል መልኩ ራሳቸውን በየጊዜው ማሻሻል እንደሚጠበቅባቸው ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል፡፡
ከተሞች ራሳቸውን በየጊዜው ማሻሻል ይኖርባቸዋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ አዲስ አበባ ላይ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ለብዙዎች የሥራ እድል የፈጠረና የከተማዋን ገፅታ በአጭር ጊዜ መቀየር ያስቻለ ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን ለአብነት አንስተዋል፡፡
