ኮሪደር ልማት ሥራ መፍጠር እና መፍጠን ዕሳቤዎችን በተግባር ያሳዩ ናቸው_ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ

ሕዳር 05/2018 ዓ.ም

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ በመልማት ላይ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን የኢፌድሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ፣የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ ሳሙኤል ሽጉጤ እንዲሁም የማዕከለዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል።

በሆሳዕና ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በመደመር መንግሥት የተቀመጡትን የመፍጠር፣ መፍጠን እና መዝለል ዕሳቤዎች ተግባራዊነት ማሳያ ናቸው ሲሉ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ።

በከተማዋ በቅርብ ዓመታት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች በከተማ ልማት፣ በከተማ ግብርና ኢኒሼቲቭ፣ በገጠር – ከተማ ትሥሥር እና በመሳሰሉት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደሆነም ተመላክቷል።

የኮሪደር ልማት ሥራ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ70 ከተሞች በላይ እየተከናወነ የሚገኝ እና እንደ አገር የላቀ ዕመርታ የታየበት መስክ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የሆሳዕና የኮሪደር ልማትን እንደ አርዓያነት የምንወስደውና ለሌሎች ክልሎች በአጭር ጊዜ መፈጸም እንደሚቻል የሚያስተምር በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

በህዝባችን ዘንድ የኮሪድር ልማት ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መጥቷል ያሉት አቶ ተስፋሁን ለዚህም ዋንኛ ምክንያት ፕሮጀክቱ በተባበረ የሕዝብ እና የመንግሥት ተሳትፎ በአጠረና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲሰራ መደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ሥራው በተግባር የህዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እና የባለቤትነት ስሜት መፍጠር በመቻሉ ሕዝቡ ኮሪደር ልማቱ እንዲመጣለት እና በየአካባቢው እንዲስፋፋለት ከፍተኛ ፍላጎት እንዲያድርበት እንዳደረገው ጠቅሰዋል ፡፡

Similar Posts