Similar Posts
ወቅታዊ መረጃ
ሃገራችን ኢትዮጵያ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ የሚካሄደውን የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ከወትሮው በላቀ መልኩ በድምቀት ለማስተናገድ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ እንግዶቿን ለመቀበል ዝግጁ ሆናለች። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ኅብረት ምስረታም ሆነ ከተመሰረተ በኋላ ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ጋር በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጋለች። የኅብረቱ መቀመጫ እንደመሆናችንም በየዓመቱ የሚካሄዱ የአስፈጻሚዎች እና የመሪዎች ስብሰባዎችን በድምቀት ስናስተናግድ ቆይተናል። የአፍሪካ ኅብረት ሃገራችን ኢትዮጵያ ለፓን…
ኢሬቻ ኢትዮጵያ ለዓለም የምታበረክተዉ ድንቅ እሴቷ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ለዓለም አበርክታለች፡፡ እሴታቸዉን ጠብቀዉ ለዘመናት በሕዝብ እየተከበሩ የዘለቁ ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላትንና ትውፊቶቻቸዉን በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ፣ የትምህርት እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የሰው ልጆች ሁሉ ሀብት ተብለው እንዲመዘገቡም አድርጋለች፡፡ ለምዝገባ በሂደት ላይ የሚገኙ በርካታ እሴቶች ባለቤትም ነች፡፡ ኢሬቻ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ በየዓመቱ የሚከበር የይቅርታ እና የምስጋና በዓል ነው፡፡…
ስኬቶቻችን የሰንደቃችን ከፍታ የሚጨምሩ ናቸው
********************************** ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት እመርታዊ ስኬቶችን እያስመዘገበች የሚመጥናትን ከፍታ እየያዘች ትገኛለች። ለዘመናት የቁጭት እና እንጉርጉሮ ትርክት ምንጭ የነበረዉን ዓባይን ገርታ የኃይል እና ብርሃን ምንጭ አድርጋለች፡፡ በንጋት ኃይቅ በምግብ ሉዓላዊነቷ ላይ ጉልህ ሚና የሚጫወት የዓሣ ምርት ማግኘት ችላለች፤ ዐዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ደሴቶችንና ከተሞችን ፈጥራለች፡፡ የዓባይን የቁጭት ትርክት ወደ ድል እና አሸናፊነት ብስራት ቀይራለች፡፡ ተጨማሪ…
“የነገዋ ኢትዮጵያችን በአስተማማኝ መሠረት ላይ እንድትቆም ወሳኝ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮቿ ላይ እየመከረች ነው።”
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን የጋራ ዘርፈ ብዙ እና ውስብስብ የሆኑ ችግሮቻቸዉን በምክክር ለመፍታት ቆራጥ ርምጃ ወስደው የተነሡበት ወቅት ነው። ሀገራችን በበርካታ ጉዳዮች በተቃርኖዎች ውስጥ ለረዥም ዘመናት ስትናጥ እና በአስከፊ ግጭቶች ውስጥ ስታልፍ ቆይታለች። በተለይም ለረዥም ዓመታት እጅግ መሠረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በፖለቲካ እና በሐሳብ መሪዎች እንዲሁም በኅብረተሰቡ ክፍሎች መካከል ልዩነት እና አለመግባባቶች ኖረዋል። እነዚህን አለመግባባቶች…
የፕሬስ መግለጫ
ኢትዮጵያዊነት ብያኔዉ የተሻለ ዓልሞ የላቀ ማሳካት ነው! ኢትዮጵያ የቀደምት ሥልጣኔ መነሻ፣ የጥቍር ሕዝቦች የነፃነት ቀንዲል ብቻ አይደለችም፤ ኢትዮጵያ የመጪዉ ትውልድ የተስፋ ምድር ጭምር ናት፡፡ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በጋራ ሉዓላዊነትን ከማስከበር ባሻገር የሚገለጹ፣ የመቻል ተምሳሌቶች ናቸው፡፡ “በጋራ እንችላለን” ብለው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን እውን አደረጉ፡፡ “በጋራ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናልብስ” ብለው ላለፉት ስድስት ዓመታት ከ40 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን…
የፕሬስ መግለጫ
ጉባኤዉ ኢትዮጵያ ልምድ ያካፈለችበት እና የመፍትሔ አካል ኾና የቀረበችበት ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ያስተናገደችዉ 2ኛዉ የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤ ልምድ ያካፈለችበት እና ለምግብ ሥርዐት መስተካከል መፍትሔዎችን ያቀረበችበት ነበር፡፡ የኢትዮጵያ እና የጣሊያን መንግሥታት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በመቀናጀት ያዘጋጁት የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤ በርካታ መሪዎች፣ የግብርናዉ ዘርፍ ተመራማሪ ግለሰቦች እና ተቋማት እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በታደሙበት በአዲስ…

