ወቅታዊ መረጃ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን በማሰብ ከነገ ሐምሌ 20 ቀን ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት ብሄራዊ የሃዘን ቀን ሆኖ እንዲታወጅ ወስኗል።
በእነዚህ ቀናት በሁሉም የሃገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች፣ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ምክር ቤቱ ወስኗል።