ዓድዋ የብሔራዊ አንድነታችን መሠረት፣ የነገው ታሪካችን ምሰሶ ነው

የካቲት 20/2018 ዓ.ም

የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓል “ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ” በሚል መሪ ቃል በድምቀት አክብሯል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ እንደገለጹት፣ ከ130 ዓመታት በፊት አባቶቻችን ለትውልድ የሚተርፍ አኩሪ ታሪክ ሰርተው እንዳስቀሩ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን በወቅቱ ድል ሊቀዳጁ የቻሉበትን ዋና ምክንያት ሲያብራሩ፣ ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ለአገር አንድነት በጋራ መቆም መቻላቸው እንደነበር ጠቅሰዋል።

አቶ ተስፋሁን አክለውም፣ አባቶቻችን ከአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ተጉዘው ድሉን ማሳካታቸው ልዩነታቸውን በመሻገራቸው መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህ የታሪክ አሻራ ዛሬም በልማት ዘርፍ ታላላቅ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ጉልበት ሆኖናል ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ዐድዋ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለሌሎች አገራትም ትልቅ ትርጉም ያለው ድል መሆኑን ገልጸው፣ የለውጡ መንግሥት ለአድዋ ድል የሚገባውን ክብር በመስጠት የሁላችንም የጋራ ድል መሆኑን በተግባር እያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም፣ የዛሬው ትውልድ የራሱ የሆነ “ዓድዋ” አለው ያሉት አቶ ተስፋሁን፣ እንደ መንግሥት ኮሙኒኬሽን በጋራ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት በመፍጠርና በአንድነት በመቆም የራሳችንን ታሪክ ለመሥራት እንነሳ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በበዓሉ አከባበር፣ ዓድዋን አስመልክቶ በመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የፌዴራል ተቋማት ክትትል ዴስክ ኃላፊ አቶ እንዳለው ሙሉዓለም የመወያያ ሰነድ አቅርበው፣ ውይይት ተደርጓል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts