የሀገሪቱን የወርቅ ክምችት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነዉ

መንግስት የኢትዮጵያን የወርቅ ክምችት ለማሳደግ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካዎችን ማስፋፋት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡
ዛሬ ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉጂ ወርቅ የማምረት ስራ ላይ የተሰማራዉን የሚድሮክ ጎልድ ኩባንያ የስራ
እንቅስቃሴን ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ኩባንያዉ በዘርፉ ቀዳሚ በመሆኑ ለኢትዮጵያ የማዕድን አከባቢ ትልቅ አስተዋጽዖ ማበርከቱን ገልፀዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ የወርቅ ሀብትን በሚገባ በማልማትና የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማረጋገጥ አዳጋች ስለነበር፣ በኮንትሮባንድ ሳቢያ ከሀገር የሚወጣዉ በርካታ የወርቅ ምርት የህገ ወጦች ሲሳይ ሆኖ ቆይቷል፡፡
አሁን ላይ መንግስት የሀገሪቱን የወርቅ ክምችት ከምንጊዜም በላይ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ በመሆኑ፣ የወርቅ ሀብትን በሰፊዉ ለማምረት በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካዎችን የማስፋፋቱ ስራ በቀጣይነት እየሰራ ይገኛል፡፡
ባለፉት ጊዚያት የሀገሪቱ የወርቅ ሀብት ያለ አግባብ ጥቅም ላይ ሲውሉ ከቆዩ ዘርፎች መካከል አንዱ እና ዋንኛዉ ነበር ፣ በአሁኑ ሰዓት ግን መንግስት በሰጠዉ ልዩ ትኩረት፣ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የወርቅ ክምችት ከቡና በልጦ የወጪ ንግድ ትልቁን ድርሻ ይዟል፡፡
ይህ ደግሞ መንግስት በማዕድን ዘርፍ የያዘዉ ግብ ቀጣይነት ያለዉ የኢኮኖሚ እድገትን የማረጋገጡ ሂደት አወንታዊ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ያመላክታል፡፡