የምጣኔ ኃብት ሪፎርም መነሻና አቅጣጫ

ሀገር በቀል የምጣኔ ኃብት ማሻሻያ ሥራዎች
አንደኛ በመንግሥት እጅ የነበሩትን የልማት ተቋማት ወደ ግሉ ዘርፍ ማስተላለፍ (Privatization)፣ ሁለተኛ የንግድ አሠራር ማሻሻያ (Ease of doing business) ሦስተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረትና የውጭ እዳ አከፋፈል ችግሮችን ለመፍታት የተሰሩ ማሻሻያዎች ናቸው።
የግሉን ዘርፍ ከመንግሥት ጋር በጋራ ለማሳተፍ በወጣው አዋጅ የግሉ ዘርፍ እንዴት ተሳትፎ ማድረግ እንደሚችል መንግሥት ዝርዝር መረጃ ሰጥቷል። ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ የግል ባንኮች ውስጥ ሼር መግዛት እንዲችሉ መፈቀዱ ለሴክተሩ እጅግ ወሳኝ ነው። ባንኮች ለግል ኢንቨስትመንቶች በተለይም ከፍተኛ የሥራ እድል ለሚፈጥረው የግብርና ዘርፍ የሚያደረጉት የካፒታል አቅርቦት ለግብርናው እና ለሎጂስቲክሱ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ የአቅርቦት ችግርን ለመፍታት እየተሰራ እንደሆነ ማሳያ ነው፡፡
