የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ታላቁን ገዥ ትርክት በጋራ ልንገነባ ይገባል

|

ሰላማዊ  ካሳ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ

ሕብረ ብሄራዊነት የተከበረባት ጠንካራ አንድነት ያላት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ታላቁን ገዥ ትርክት በጋራ ልንገነባ ይገባል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊ  ካሳ ተናገሩ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ዛሬ በጀመሩት ውይይት ሚኒስትር ዴኤታዋ እንዳሉት እንደ መንግስት ኮሙኒኬሽን አመራርና ባለሙያ ለሃገራዊ ግንባታ አዎንታዊ ገዥ ትርክትን መገንባት ትልቅ ኃላፊነት የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ባለሙያዎች ይሆናል፡፡

የነጠላ እና የገዥ ትርክትን ጽንሰ ሀሳብን ጉዳይ ከስር ማወቅና ለሃገራዊ ግንባታ በሚረዳ መልኩ ማስረጽ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች እንደሚጠበቅ የተናገሩት ሚኒስትር ዴታዋ ትርክት የአብሮነት ታሪካዊ መሰረት እንደሆነም አንስተዋል፡፡

ትርክት የወደፊት ተስፋን ዛሬ ላይ የሚኖረንን ሚና እንዲሁም ነገ የሚከሰቱ ክስተቶችን የምናይበት መሆኑን ሰላማዊት ካሳ ጠቁመው ትርክት የሰዎችን ማንነት እንደሚፈጥር፣ሰዎች ለአብሮነታቸው ትርጓሜ የሚገለጽበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ነጠላ እና ገዥ ትርክት መኖሩን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታዋ ነጠላ ትርክት የተወሰኑ የማህበረስብ ክፍሎችን ነጥሎ ጀግና ወይንም ተወካዮች አድርጎ አንድን ማህበረሰብ በመወከል የሚሰራ መሆኑንና ገዥ ትርክት ግን አንድን ማህበረሰብ በሰፊው ምሉዕ እና በዋናነት በተለያዩ መዋቅሮች ውስጥ ማስረጽ የሰዎችን አስተሳሰብ እና እውቀት ቅርጽ የሚሰጥ እንደሆነ አስምረውበታል፡፡

በውይይቱ የትክርት ምንነት፣የተራራቀው የሃገራችንን ትርክት፣ገዥ ትርክታችንን እንዴት እንገንባ፣የአሉታዊ ትርክት አደጋዎች እና ብሄራዊ ትርክትን ማጽናት የሚሉ ርዕሶች ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል፡፡

Similar Posts