የአፍሪካ-ጣሊያን ጉባኤ በአፍሪካ አፈር ሲካሄድ የመጀመሪያ መዳረሻውን ኢትዮጵያ አድርጓል

የአፍሪካ-ጣሊያን ጉባኤ በኢትዮጵያ መካሄዱ የአፍሪካ-ጣሊያን ግንኙነት በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የትብብር ማዕቀፎች ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያደርግ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የአፍሪካ-ጣሊያን ፎረም መካሄድ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከሮም ውጭ ሲካሄድ ይህ የመጀመሪያው ነው ያሉት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ በአፍሪካ አፈር ሲካሄድ የመጀመሪያዋ መዳረሻ ኢትዮጵያ መሆኗ ሀገራችን አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ከማስተሳሰር አንጻር ያላትን ከፍተኛ አቅም የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2024 በሮም ይፋ የተደረገውን የማቴይ ዕቅድ አፈጻጸም መገምገም እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ማዕከላዊ አጀንዳ ያደረገው የአፍሪካ-ጣሊያን ጉባኤ፣ ከአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ አስቀድሞ የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚካሄድም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የጉባኤው ዋና ዋና አምዶች በሆኑት ኢነርጂ፣ ግብርና፣ ትምህርትና ስልጠና፣ ጤና፣ ውሃ እና መሠረተ ልማት ላይ በርካታ ተሞክሮዎችን ማቅረብና አጋርነቶችን ለመመስረት የሚያስችላት ቁመና ላይ እንደምትገኝም አሳውቀዋል፡፡

በመጨረሻም እነዚህን ጉባዔዎች ለመዘገብ ከ800 በላይ የሚዲያ ባለሞያዎች ፈቃድ ጠይቃቸዉን ገልጸዉ፣ ርዕሰ ብሔሮች፣ ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ ምክትሎች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ17 ሺህ በላይ የልዑካን ቡድን አባላት በአፍሪካ-ጣሊያን ጉባኤ እና በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts