የኮሪደር ልማት ሥራችን ከተሞችን ውብ ገጽታ ከማላበስ የተሻገረ ነው ።

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የኮሪደር ልማት የከተማን ስታንዳርድ ለማስጠበቅ ዕድል የፈጠረ የከተማ መልሶ ግንባታ የ(Rehabilitation )ሥራ አካል ነው ።

በኮሪደር ልማት ከተሞች የፍሳሽ መስመር ደረጃዎች እንዲሻሻል ፣የመሠረተ ልማት አውታሮችን (የቴሌ፣ የውሃ ፣ የመብራት .. ወዘተ) እንዲቀናጁ ፣የከተሞች ፕላን እና የህንፃዎች ንፅህና፣ ውበት፣ ቀለም፣ መብራት ደረጃ እና ስታንዳርድን ለማስጠበቅ አስችሏል ።

በኮሪደር ልማቱ የተሠሩ የብስክሌት መንገዶች ለህብረተሰቡ ተጨማሪ የትራንስፖርት አማራጭን

የሰጡ ሲሆን የመኪና የፓርኪንግ ቦታዎች ፣

ተርሚናሎች፣ ምቹ እና ዘላቂ የእግረኛ መንገዶች የአረንጓዴ ቦታዎች እና የሕዝብ መዝናኛዎችና ማረፊያዎች ተገንብተዋል ።

የኮሪደር ልማት ሥራችን ኢትዮጵያ ብርሀናማ ከተሞች እንዲኖራት አስችሏል ። በቀንና በማታ የሚሰራ አመራርና ሠራተኞች በመፍጠር በኢትዮጵያ አዲስ የሥራ ባህልን አስተዋውቋል።

የኮሪደር ልማት ለበርካታ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፣ የፕሮጀክት አፈፃፀም ልምድን በእጅጉ ቀይሯል፣ የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን አሻሽሏል፣ የሀገር ውስጥ ተቋራጮች አቅም እንዲፈጥሩ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያግዝ ምቹ መደላድል መፍጠር ተችሏል ።

በአጠቃላይ የኮሪደር ልማቱ የከተማ ስታንዳርድ ደረጃን በማስጠበቅ፣ ከተሞች ንጹሕ ፣ ውብ እና ለነዋሪዎችና ለቱሪስቶች ምቹ እና ተመራጭ እዲሆኑ በእጅጉ ያገዘ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት እና የተግባር አመራር በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ተሳትፎ እና ቅንጅት ከተሞችን እየለወጠ የሚገኝ ታላቅ ፕሮጀክት ነው።

#ቪዲዮ_አዳማ_ከተማ_ኮሪደር

Similar Posts