የኮሪደር ልማት ግንባታ ያካተታቸው የመሰረተ ልማቶች፦
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ያቀፋቸዉ መሰረተ ልማቶች
-በዚህ ኘሮጀክት ላይ ከ48 ኪ.ሜ በላይ የተሽከርካሪ የመንገድ ልማት
-4 የመሬት ውስጥ የእግረኛ መንገዶች፣
-96 ኪ.ሜ ሰፋፊ የእግረኛና 100 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገዶች፣
-5 ኪ.ሜ የመሮጫ ትራክ
-48 የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን የሚያሳልጡ የአውቶቡስ እና የታክሲ ተርሚናሎችንና መጫኛ ማውረጃ ስፍራዎች፣ በጥቅሉ ከ 240 ኪ.ሜ በላይ የሚሆን የመንገድ እና ተያያዥ መሰረተ ልማት፤
-70 የከተማን ውበት የሚጨምሩ የህዝብ መናፈሻ ስፍራዎች፣ ፋውንቴኖችና የአረንጓዴ ስፍራዎች፣ የመዝናኛና የመናፈሻ ስፍራዎች፣ የልጆች መጫዎቻና የህዝብ ፕላዛዎች፣
-120 የሚሆኑ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የፍሳሽ ማስተላለፊያዎች፣ ከተማችንን የሚመጥኑ የደህንነት ካሜራዎች፣ የብልህ ትራንስፖርት ስርዓት ( intelligent transport system) በመሬት ውስጥ የመዘርጋት ስራ ፣
-ከ400 በላይ ህንጻዎች እንዲታደሱ የማድረግ እንዲሁም የከተማዋን ደረጃ የሚመጥኑ የቀለምና የመብራት ስራዎች እና ሌሎች በርካታ ግንባታዎችን በመከናወን ላይ ይገኛሉ::
