የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤን በመለወጥ የተሟላ ብልጽግና ማረጋገጥን ያለመ ነው።

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ጥቅምት 22/2018

መንግሥት ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማን ለመገንባት የኮሪደር ልማቱን ከአዲስ አበባ በመጀመር በሁሉም ክልሎች እንዲስፋፉ የሚያደረጉ ከተማን የማልማት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡

የኮሪደር ልማት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ከማረጋገጥ አኳያ የጎላ ሚና አበርክቷል ፡፡ በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ቀስበቀስ የሁሉም ከተሞች ልምድና ባህል ወደ መሆን ተሸጋግሯል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከኮሪደር ልማቱ በፊት ምን እንደምትመስል እና ከኮሪደሩ የመጀመሪያ ዙር ልማት መጠናቀቅ በኋላ ያላትን ውብ ገጽታ በመመልከት በመላዉ ኢትዮጵያ 68 ከተሞች ላይ የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ይገኛል ፡፡

የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሳሳረ ልማት ነው። ልማቱ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ ልማት ለዜጎች ለማቅረብ በማለም የተከናወነ ሲሆን ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ ሊሆን በሚችል መልኩ ከተሞች እያለሙ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ህዝብ ገጠር የሚኖር በመሆኑ የዜጎችን ህይወት በተሟላ መልኩ ለመቀየር እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በከተማ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ በከተሞች የታየዉ አመርቂ ዉጤት በገጠርም መታየት አለበት፡

ከዚህ አንጻር የኮሪደር ልማቱ በከተማ ብቻ ሳይገደብ የገጠሩን ማኅበረሰብ አኗኗርን ለማሻሻል የገጠር ኮሪደር ልማት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2017 ግንቦት ወር መጨረሻ የገጠር ኮሪደር ልማት አካል የሆነውን ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታ አስጀምረዋል ።

የተሻላ ኑሮን ፍለጋ ከከተማ ወደ ገጠር የሚደረገዉን ፍልሰት በመቀነስ የተመጣጠነ ዕድገት በሁሉም አካባቢ ለማምጣት የገጠር ኮሪደር ልማት ተግባራዊ ማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው ፡፡

የገጠር ኮሪደር ልማት የተስተካከለ ኑሮን እና ከተሜነትን ወደ ገጠር ያመጣል ። በገጠር የሚገነቡ ሞዴል መንደሮቹ ቀላል ወጪ በሚጠይቁና በአካባቢው በሚገኙ ግብዓቶች የሚገነቡ ከመሆናቸውም በላይ አርሶ አደሩ ጤናማ እና ክብር ያለውን ህይወት እንዲኖር የሚያስችሉ ናቸው ።

የገጠር ኮሪደር ልማት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ስነ ምህዳራዊ ፋይዳን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ይህም ዘላቂ ልማትና የተረጋጋ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ።

ከለዉጡ በፊት የኢኮኖሚ ምንጭ የሆነው የገጠሩ አካባቢ ትኩረት ተነፍጎት የቆያ በመሆኑ የተሻለ ኑሮን ፍለጋ ወደ ከተማ የሚሄደው ወጣት ቁጥር ከፍተኛ የነበረ ሲሆን ዛሬ ላይ በሚኖርበት አካባቢ ተረጋግቶ እሴት መጨመር ላይ እየሰራ እንዲኖር የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር ተችሏል።

የገጠር ኮሪደር በውጤት ደረጃ የኅብረተሰብ ሽግግርን የሚያመጣ እና የመሰረተ ልማትን ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ጉዳዮችን ያቀፈ ሲሆን፤ በገጠር አካባቢዎች ዘመናዊ አኗኗርን የሚፈጥር እና የአርሶ አደሩን ህይወት የሚቀይር ሀገራዊ ውጥን ነው ።

በጥቅሉ ልማቱ አርሶ አደሩ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚና ዘመናዊ ስልተ-ምርት እንዲከተል የሚያደርግ አዲስ የአኗኗር ባህልን የሚተክል ሲሆን እንደሀገር የከተማ ፍልሰትንና የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ምቹ ዐውድን የሚፈጥር ነው።

Similar Posts