የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“አርሶአደሮቻችን እያመረቱ ብቻ አይደለም፤ ከመዋጮዎቻቸውም እሴት እያፈሩ ይገኛሉ። በ1996 ዓ.ም የተመሠረተው የጊቤ ዲዴሳ የገበሬዎች የኅብረት ሥራ ማኅበር 207 የመጀመሪያ ደረጃ ማኅበራትን ያቀፈ ነው።

አንድ መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ ገበሬዎችን የሚያገለግለው ማኅበሩ፤ አሁን ላይ የግብርና ግብዓቶችን ከማቅረብ ተሻግሮ የምርት እሴትን ወደመጨመር አሳድጓል። ማኅበሩ በቅርቡ ዘመናዊ የእህል ወፍጮ ያቋቋመ ሲሆን በቀን 1200 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት የማምረት አቅም አለው። በ2.8 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባው ፋብሪካ ለአካባቢው ጊዜያዊ እና ቋሚ የሥራ እድሎችን ፈጥሯል።”

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts