የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

‎”የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀውና ባለፉት ዓመታት በሚዲያ ዘርፍና ተቋማት ላይ የተመዘገቡ ስኬቶች በቀረቡበት የምክክር መድረክ ላይ ታድሜ ሀሳቤን አጋርቻለሁ።

‎ባለፉት ስምንት ዓመታት የሚዲያ ምህዳሩን በዲሞክራሲያዊ አውድ ለመዋጀት በወሰድነው እርምጃ ለሀገር ግንባታ የሚረዳ መሠረት ጥሏል። ይህ ውጤት እንዲቀጥልም ሚዲያዎች ከዋልታ ረገጥነትና ከጽንፈኝነት ወጥተው በእውነት ላይ የተመሠረተ ትርክት በመገንባት፣ ለጋራ ማንነትና ለብሔራዊ መግባባት በቁርጠኝነት ሊሠሩ ይገባል።

‎ሚዲያዎቻችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በጥናት የታገዘ ጥልቅ ትንተና በማቅረብ፣ ከአርዕስት ሽያጭ ባለፈ ለሀገር አጀንዳዎች ትኩረት መስጠት ይኖርባቸዋል። ተግባራቸውም በዓላማ፣ በእይታ፣ በሙያዊ ብቃትና ለህዝብ ቅርብ በመሆን ላይ ተመስርቶ፣ ሚዛናዊነትን በጠበቀ መልኩ ለሀገር ብልጽግና መንገድ ጠራጊና ችግር ፈቺ ሆነው ሊቀጥሉ ይገባል።”

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts