የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ ላይ በግልጽ የተቀመጠውን አካታች፣ ዘላቂ፣ ሰው ተኮር የከተማ ልማት ጽኑ አቋማችንን የኮሪደር ልማት ሥራችን ያንፀባረቀ ሆኗል። ከአዲስ አበባ ባሻገር በተለያዩ ከተሞቻችን የተተገበረው ሥራ የከተማ እንቅስቃሴን ያሻሻለ፤ ሕዝባዊ ስፍራዎችን እንደገና ያበለፀገ፤ የየአካባቢውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ያጠናከረ እና የአካባቢን ለለውጥ አይበገሬነት ከፍ ያደረገ ነው። የመኖሪያ መንደሮችን በማቆራኘት እና በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ከተሞችን የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ አቅም በማውጣት የተተገበረው ጥረት ግልጽ ሀገራዊ ርዕይን ያሳያል። ይኽ ርዕይ ለመኖር ምቹ፣ ተወዳዳሪ እና አካታች ሆነው በመላው ኢትዮጵያ የተመጣጠነ ልማት እና የጋራ ብልጽግና የተረጋገጠባቸው ከተሞችን የመገንባት ርዕይ ነው።”

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፡-

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts