የፀና ዲፕሎሲያዊ ልህቀት በሉአላዊት ኢትዮጵያ
የፀና ዲፕሎሲያዊ ልህቀት በሉአላዊት ኢትዮጵያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዓለም ጥንታዊት ሀገር የላቀ ክብር የሰጡኝ ታላቅ የኒሻን ክብር፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ የተበረከተልኝ እዉቅናና ሽልማት እንደሆነ እገነዘባለሁ፡፡
ይህንን የክብር እዉቅናና ስጦታ በብዙ ሰብአዊነት እና የሕንድ ህዝብ ምስጋና አድርጌ እቀበላለሁ፡፡ ሽልማቱም የተሰጠዉ የሁለቱን ወዳጃዊ አጋርነታችንን የቀረጹ እና ትልቅ ድርሻ ላበረከቱ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ሕንዳውያን ነው፡፡
በደቡብ አፍሪካ በተካሄደዉ የጂ20 ጉባኤ ላይ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጣ ግብዣ ላደረገለኝ ጓደኛዬን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
አሁን ላይ የዓለም ትኩረት በዓለም አቀፍ የደቡብ-ደቡብ ትብብር ላይ በሆነበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ ዘመን የማይሽራቸው ወጎች፣ ክብር፣ ነፃነት እና በራስ መተማመን ላይ ያተኮረው ለሁላችንም ራስን የመቻል ሚስጥር፣ እንዲሁም በሁሉም መስኮች ሉዓላዊነትን ማስከበር እንደሚቻል በተግባር አሳይታለች፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ራዕይ መሪነት ስር፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ተደማጭነትንና ተገቢዉን ቦታ እያገኘች ነው፡፡ ለሕንድ ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ደማቅ ድፕሎማሲያዊ አቀባበል መደረጉ የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ፖሊሲ ጠንካራ መሆኑን በግልጽ አመላካች ነዉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባለፉት የመንግሥት ሥርዓቶች እና በዘመናዊ የኢኮኖሚ ግቦች መካከል ያለውን ክፍተት በማጥበብ ትክክለኛ ብልጽግና በእኩልነትና አካታችነት ላይ የተገነባ መሆኑን እያረጋገጡ ነው፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያደረኩት ጉብኝት ከድፕሎማሲ ባሻገር ነዉ፡፡ የሕንድና የኢትዮጵያ ግንኙነት፣ ቀጣይ የዕድገት፣ የፈጠራ እና የአለም አቀፍ ትብብር ምልክት ለማድረግ ያለን ቁርጠኝነት ወደ ላቀ ደረጃ መሸጋገሩን የሚያሳይ ነው፡፡
የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ
ተጨማሪ መረጃ
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication






