የፕሪቶሪያ ስምምነት መነሻና መድረሻው ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ተቋማትን ማክበር ነው!






ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ የሚገለጽ ብዝኃነት ባለቤት ናት፡፡ የቋንቋ፣ የባህል፣ የብሔር፣ የሃይማኖት፣ የፖለቲካዊ አመለካከት፣ የዕድሜ፣ የፆታ ወ.ዘ.ተ ብዝኃነቶቿ የሚያስጌጧት ድንቅና ቀደምት ሀገር ናት፤ ኢትዮጵያ፡፡ ይህንን ብዝኃነቷን እንደ እሴት የምታዳብርበት፣ እሴቱን ወደ መፈጸም ዐቅም የምትለውጥበት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐት ባለቤትም ናት፡፡ ለዚህም ነው የጋራ የቃል ኪዳን ሰነድ በሆነው ሕገ መንግሥታችን አንድ የጋራ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመገንባት በነፃ…
የአማራ ክልል ሕዝብ ባለፉት ጥቂት ዓመታት መክፈል የማይገባዉን ውድ ዋጋ በጥቂት ጥቅመኞች ምክንያት እየከፈለ ይገኛል፡፡ የፋኖን ታሪካዊ አነሣሥ እና ዓላማ ባልተከተለ አግባብ ራሳቸዉን በፋኖ ስም የሚጠሩ ፅንፈኛ ኃይሎች በቀሰቀሱት ግጭት የአማራ ክልል ሰላም እና ልማት ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ ፋኖ ሀገር በባዕድ ወራሪ እጅ በወደቀችበት እና ማእከላዊ መንግሥት በግዞት በቆየበት ወቅት ሀገርን ለማዳን የተደረገ ተጋድሎ የተመራበት ድንቅ…
ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ ብዝኃ ማንነት ደምቃ፣ ፀንታና ታፍራ የኖረች፣ ብዝኃ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት የሆነች ድንቅ ሀገር ናት፡፡ ብዝኃነታችን የጥንካሬያችን፣ የሥልጣኔያችን፣ የአይበገሬነታችን፣ የክብራችን፣ የነፃነታችን እና የአልሸነፍ ባይነታችን ምሥጢር ነው፡፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙ ጥንታዊ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ቦታዎች እና የኪነ ሕንጻ ሀብቶቻችን የብዝኃነታችን ውጤቶች ናቸው፡፡ የአክሱም ሐውልቶች፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የለጋ ኦዳ ዋሻ…
ዓድዋ ድላችንም ቅርሳችንም ነው! ኢትዮጵያ ጠንካራ ሥርዓተ መንግሥትና የጥንታዊ ሥልጣኔ ማዕከል ከነበሩ ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች፡፡ በዚህ ረዥም የታሪክ ጉዞ ኢትዮጵያ ሀገራችን ባሳለፈቻቸው የታሪክ ምዕራፎች ሁሉ ነፃነቷንና ሉዓላዊነቷን ለመጣስ ተከታታይ ወረራዎች ተፈጽመውባታል።ይሁን እንጂ የተቃጡባትን ወረራዎችና ጦርነቶች በአኩሪ ተጋድሎና መስዋዕትነት በመመከት የዓለማችን የነፃነት ቀንዲል ለመሆን በቅታለች። ሕዝቦቿ የሰውን ሀገር ግዛት ወርረው የማያውቁና የራሳቸውንም ስንዝር መሬት…
ኢትዮጵያ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ለዓለም አበርክታለች፡፡ እሴታቸዉን ጠብቀዉ ለዘመናት በሕዝብ እየተከበሩ የዘለቁ ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላትንና ትውፊቶቻቸዉን በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ፣ የትምህርት እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የሰው ልጆች ሁሉ ሀብት ተብለው እንዲመዘገቡም አድርጋለች፡፡ ለምዝገባ በሂደት ላይ የሚገኙ በርካታ እሴቶች ባለቤትም ነች፡፡ ኢሬቻ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ በየዓመቱ የሚከበር የይቅርታ እና የምስጋና በዓል ነው፡፡…
ኢትዮጵያ ነገዋን ዛሬ ላይ ለመሥራት እያደረገች ያለውን ጥረት እና የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስተዋወቅ 5ኛዉን የጳጉሜን ቀን “የነገዉ ቀን” በሚል ስያሜ እና “ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” በሚል መሪ መልእክት እያከበረች ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከራሷ ባሻገር የአፍሪካን ማንሰራራት ለማብሰር ዛሬ ላይ ነገዋን እየሠራች ነው፡፡ ለአምስተኛዉ የኢንዱስትሪ አቢዮት የሚመጥን ትውልድ መቅረጽን፣ ለኢንዱስትሪ ዕድገቱ የሚመጥን ታዳሻ ኃይል ማቅረብን፣ የዘመኑ ከተሞችን መፍጠርን፣…