ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የታደሰውን የፋሲል ጊቢ መርቀዋል።
የተከናወነው ሰፊ የእድሳት ሥራ በቅርስ ስፍራው ነባሩን ታሪክ በመጠበቅ ውበቱን እና ተደራሽነቱን በማሻሻል አዲስ እስትንፋስ የሰጠ ሆኗል።
የእድሳት ሥራው የቤተመንግሥቱን የግንባታ መዋቅር መጠገን፣ የእግር መንገዶችን ማሻሻል፣ ቁልፍ የሆኑ ሕንፃዎችን ከዝግባ እና ዋንዛ በባሕላዊ ቁሳቁሶችን ተጠቅሞ በማደስ የስፍራውን ግለ ወጥ መልክ እና ባሕርይ ለመጠበቅ ተሰርቷል።
ለጎብኝዎች ምቾት የተሰናዱ አገልግሎት መስጫዎችም ትርጉም ባለው ደረጃ ተሻሽለዋል። አዲስ የቱሪስት ማዕከልም ተከፍቷል። ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶች፣ የተሻሻሉ የመብራት እና የደኅንነት ሥርዓቶችም ተሰናድተዋል።
እንደ አፄ ፋሲል፣ አፄ ቀዳማዊ ዮሃንስ እና አፄ ቀዳማዊ ኢያሱ አቢያተ መንግሥት ብሎም ድልድዮች፣ መታጠቢያ ሥፍራዎች፣ ታሪካዊ በሮች ወዘተ በጥንቃቄ ታድሰዋል።
በተጨማሪም ከ40,000 ስኴር ሜትር በላይ የአካባቢው ምድር የማስዋብ ሥራ ተሰርቷል። ይኸም ለጎብኝዎች ይበልጥ ሳቢ የሆነ ከባቢ ፈጥሯል። አጠቃላይ የእድሳት ሥራው ከአንድ አመት በታች የፈጀ ሲሆን የዚህን አስደናቂ የታሪክ እና የባሕል ሥፍራ ለረዥም ጊዜ ጠብቆ በሚያቆይ አኳኋን ተከናውኗል።
Prime Minister Abiy Ahmed and First Lady Zinash Tayachew, together with senior federal and regional officials, officially inaugurated the restored Fasil Ghebbi. The extensive restoration project has breathed new life into this treasured heritage site, preserving its history while enhancing its beauty and accessibility. The work included repairing palace structures, improving pathways, and carefully restoring key buildings using traditional materials such as cedar and wanza wood to maintain the site’s authentic character. Visitor amenities have also been significantly upgraded, with a new tourist center, modern public restrooms, and improved lighting and security systems. Several iconic landmarks, including the palaces of Emperors Fasil, Yohannes I, and Eyasu I, along with nearby bridges, baths, and historic gates, have all been meticulously renovated. In addition, over 40,000 square meters of the site have been landscaped, adding greenery and creating a more inviting atmosphere for visitors. The entire restoration was completed within just one year, ensuring the long-term preservation of this remarkable cultural heritage site.


















