ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችና ማኅበረሰብን አጽናኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እስካሁን የ231 ዜጎችን ሕይወት እንደቀጠፈ በተረጋገጠው የጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችና ማኅበረሰብ በአካል ለማፅናናት በስፍራው ተገኝተዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር። እና ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ ከቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ከሌሎች ከፍተኛ የፌደራል መንግሥት አመራሮች ጋር በስፍራው ሲገኙ በክልል ሃላፊዎች እና በማህበረሰቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

Similar Posts