ኢትዮጵያ ለማንሰራራት የሚስችላትን ከፍታ ይዛለች!

ኢትዮጵያ በሚመጥናት ከፍታ ልክ የሚያስቀምጣትን የማንሰራራት ጉዞ ጀምራለች፡፡ በጊዜ ምሕዋር ውስጥ ሲያጋጥሟት የነበሩ አንጋዳዎችን በብስለት እየተሻገረች ከፍታዋን በመያዝ ላይ ናት፡፡ የአይችሉም ትርክትን በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሰብራለች፤ ብርሃንን ለምሥራቅ አፍሪካ ፈንጥቃለች፡፡ ያለማንም ዕርዳታ በኢትዮጵያውያን ሀብት፣ ድካም፣ ዕውቀትና ጥረት ሕዳሴን በማጠናቀቅ ኢንዱስትሪዎቿን በበቂ ታዳሽ ኃይል የምታንቀሳቀስ፣ ከዚያም አልፎ ለጎረቤት አገራት የምታጋራ ኾናለች፡፡ በውኃ ሀብቶቿ በፍትሐዊነት በመጠቀም ዐዲስ…