ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የታደሰውን የፋሲል ጊቢ መርቀዋል።

የተከናወነው ሰፊ የእድሳት ሥራ በቅርስ ስፍራው ነባሩን ታሪክ በመጠበቅ ውበቱን እና ተደራሽነቱን በማሻሻል አዲስ እስትንፋስ የሰጠ ሆኗል። የእድሳት ሥራው የቤተመንግሥቱን የግንባታ መዋቅር መጠገን፣ የእግር መንገዶችን ማሻሻል፣ ቁልፍ የሆኑ ሕንፃዎችን ከዝግባ እና ዋንዛ በባሕላዊ ቁሳቁሶችን ተጠቅሞ በማደስ የስፍራውን ግለ ወጥ መልክ እና ባሕርይ ለመጠበቅ ተሰርቷል። ለጎብኝዎች ምቾት የተሰናዱ አገልግሎት መስጫዎችም ትርጉም ባለው ደረጃ ተሻሽለዋል። አዲስ የቱሪስት…

“ጉልበት ይሸሻል፣ ጊዜ ይሸሻል፣ ስልጣን ይሸሻል፣ ሁሉ አላፊ ነው ፣ የማያልፈው እንደዚህ ያለው ታላቅ ስራ ነው።”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

“በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል። ፕሮጀክቱ 870 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን 17000 ሄክታር መሬት በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል። የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ መልኩ ተጠናቋል። የቀሩት ሥራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ ይገኛሉ። የመገጭ ግድብም በሚጠናቀቅበት ወቅት የአካባቢውን የግብርና ምርታማነት የሚያሳድግ ይሆናል። Daawwannaa…

በመገጭ የመስኖ ፕሮጀክት የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ መልኩ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሙሉ መልዕክት :- “በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል። ፕሮጀክቱ 870 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን 17000 ሄክታር መሬት በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል። የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ መልኩ ተጠናቋል። የቀሩት ሥራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ ይገኛሉ። የመገጭ ግድብም በሚጠናቀቅበት ወቅት የአካባቢውን የግብርና ምርታማነት…

ኢትዮጵያ የጂኦ-ቱሪዝም እምቅ ሀብቶቿን በዩኔስኮ በማስመዝገብ ተጠቃሚነቷን ለማሳደግ ተዘጋጅታልች

በኢትዮጵያ የጂኦ-ቱሪዝም እምቅ ሀብቶቿን በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የጂኦ-ፓርክነት በማስመዝገብ ተጠቃሚነቷን ለማሳደግ የዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ። ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላት ያልተነካ ሀብት በጂኦ-ቱሪዝም ተመራጭ ሀገር የሚያድርጋት ነው። ከዚህ አንጻር ለዩኔስኮ በወደፊቱ ሊቀርቡ የሚችሉ በርካታ የሀገሪቱ እጩ የጂኦ-ቅርስ ቦታዎች ተለይተዋል። ከነዚህም ውስጥ በባሌ ወረዳ የሚገኘው ሶፍ-ዑመር ዋሻ፣ በቡታጅራ-ስልጤ የሚገኙት አፈጣጠሮች፣ የሰሜንና የገራልታ ተራሮች፣ የደናክል ስምጥ ሸለቆ፣ ኤርታ…

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብራቸውን ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የንግድ፣ ኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ኢንቨስትመንት ፎረም ዛሬ በፈረንሳይ ፓሪስ መካሄድ በጀመረበት ወቅት ነው። በመክፈቻው ስነ ስርዓት ላይ ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ ክቡር የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ የአውሮፓ ኮሚሽን የአፍሪካ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጌዛ ስትራመር፣ የፈረንሳይ የወጪ ንግድ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር…

የኮሪደር ልማት ሥራችን ከተሞችን ውብ ገጽታ ከማላበስ የተሻገረ ነው ።

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የኮሪደር ልማት የከተማን ስታንዳርድ ለማስጠበቅ ዕድል የፈጠረ የከተማ መልሶ ግንባታ የ(Rehabilitation )ሥራ አካል ነው ። በኮሪደር ልማት ከተሞች የፍሳሽ መስመር ደረጃዎች እንዲሻሻል ፣የመሠረተ ልማት አውታሮችን (የቴሌ፣ የውሃ ፣ የመብራት .. ወዘተ) እንዲቀናጁ ፣የከተሞች ፕላን እና የህንፃዎች ንፅህና፣ ውበት፣ ቀለም፣ መብራት ደረጃ እና ስታንዳርድን ለማስጠበቅ አስችሏል ። በኮሪደር ልማቱ የተሠሩ የብስክሌት መንገዶች…

የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤን በመለወጥ የተሟላ ብልጽግና ማረጋገጥን ያለመ ነው።

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጥቅምት 22/2018 መንግሥት ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማን ለመገንባት የኮሪደር ልማቱን ከአዲስ አበባ በመጀመር በሁሉም ክልሎች እንዲስፋፉ የሚያደረጉ ከተማን የማልማት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ የኮሪደር ልማት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ከማረጋገጥ አኳያ የጎላ ሚና አበርክቷል ፡፡ በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ቀስበቀስ የሁሉም ከተሞች ልምድና ባህል ወደ መሆን ተሸጋግሯል ። የአዲስ አበባ ከተማ ከኮሪደር ልማቱ በፊት…