የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
“ባለፉት ዓመታት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር ሂደቱ ወደፊት እንዲራመድ በትዕግስት እና ከፍ ባለ የሞያ ስነ-ምግባር በማከናወን አሁን ያለበት ምዕራፍ ያደረሱትን ሁሉንም ኮሚሽነሮች አመሰግናለሁ። የምክክር ባህል እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት እጅግ አስፈላጊ ነው። ጠንካራ የሲቪክ ማኅበረሰብ ባህል ግንባታ ደግሞ ያላሰለሰ የመነጋገር ልምምድ እና የሰከነ የወል መደማመጥን ግድ ይላል። የእስካሁን ሂደቱም በማኅበረሰባችን በየደረጃው የመደማመጥን ከፍ ያለ…
