ፈታናዎችን በመገንዘብና የመሻገሪያ መንገዶችን ለመተለም ዜጎች ምንጊዜም ንቁ መሆን አለባቸዉ- ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
በመጪዉ ዓመት የሚኖሩ ፈታናዎችን አስቀድሞ በመገንዘብና የመሻገሪያ መንገዶችን ለመተለም ዜጎች ምንጊዜም ንቁ መሆን አለባቸዉ ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ የዘንድሮ የጷጉሜን ቀናት ስያሜን ተንተርሶ በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም የተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት ሀገሪቱ ዉስብስብ ችግሮችን በመሻገር በሁሉም ዘርፎች አኩሪና እምርታዊ ድሎች ያስመዘገበችበት ዓመት እንደ ነበር አስታዉሰዋል፡፡…
