በኢትዮጵያ በዲጂታል ጤናው ዘርፍ፣ በሰው ሀብት ልማት እና በጤና ፋይናንስ ማሻሻያ ስራዎች ዙሪያ ተጨባጭ ለዉጦች ተመዝግበዋል ፡፡
የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ከክልል ጤና ቢሮዎችና የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 27ኛው ዓመታዊ የጤና ሴክተር የምክክር ጉባኤ ካዘሬ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም በጅማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡ ጉባኤዉ በሀገር አቀፍ የጤና ግቦችና እና የማሻሻያ ክንዉኖችን፣ እንዲሁም ቀጣይ የዘርፉ አቅጣጫዎችን ለመገምገም ዓላማ ያደረገ ሲሆን፣ በተለይም በመንግስትና ባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራርን ከማጎልበት ባሻገር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጠራን…

