የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ዛሬ ጠዋት ጂቡቲ ስደርስ ክቡር ፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ አቀባበል አድርገውልኛል። ውይይታችን በጆኦፖለቲካል ጉዳዮች፣ በቀጠናዊ ሰላም እና ፀጥታ ብሎም የሁለትዮሽ ትብብራችንን በተለይም በንግድ፣ ሎጂስቲክስ እና የልማት ሥራዎች በምናጠናክርበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር። ይኽም ለሰላም እና መረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ትስስር እና የጋራ ብልጽግና ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያመለክት ነው። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮችhttps://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቢሾፍቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ ያደረጉት ንግግር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቢሾፍቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ ያደረጉት ንግግር

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

ኢትዮጵያ እምቅ አቅሟን እና ታላቅ ርዕይዋን የሚመጥን ሌላ ተጨማሪ ሜጋ ፕሮጀክት ጀምራለች።

የቢሾፍቱ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የአውሮፕላን ማረፊያውን ግንባታ ይፋዊ በሆነ መርሃ ግብር ዛሬ በስፍራው አስጀምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው እለቱ ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊነት እና ብልጽግና የምታደርገው ጉዞ አንድ እጥፋት ነው በማለት ገልጸውታል። የኢትዮጵያ…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ80 አመት አፍላ ወጣት ነው

መቀመጫው የአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአመት 25 ሚሊዮን ተጓዦችን በማስተናገድ በእጅጉ ተጨናንቋል። በ160 በላይ ዘመናዊ አውሮፕላኖች (በቅርቡ 60 አዲስ አውሮፕላኖች ይጨመራሉ) ወደ 145 በላይ መዳረሻዎች መብረር ሲታሰብ አንድ አውሮፕላን ጣቢያ እንደማይበቃ ግልጽ ይሆናል። ስለዚህም ተጨማሪ ማረፊያ መሥራት ይገባል። ትልቅ ታሪክ። የላቀ ትስስር። የላቀ እቅድ። PMOEthiopia ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮችhttps://linktr.ee/FDREGovermentCommunication