Similar Posts
የፖሊሲ ጉዳይ ቅኝት – ሐምሌ 3፣ 2018 ዓ.ም
#PMOEthiopia Post Views: 44
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የራስን ሀብት በራስ ዐቅም ማሳካት እንደሚቻል የሚያሳይ ዐዲስ የፓንአፍሪካኒዝም አብነት ነው፡- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ታላቁ የኢትዮጵያ ግድብ ከኃይል ማመንጫ ግድብነት ባሻገር በራስ ዐቅም የራስን መሻት ማሳካት እንደሚቻል ያሳየ ዐዲስ የፓን አፍሪካኒዝም አብነት መኾኑን የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ተናገሩ፡፡ ሚኒስትር ዲኤታዉ አርቲ አፍሪካ ባዘጋጀዉ የአፍሪካ የሚዲያ ዕውቅና መድረክ ዋዜማ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝም ማእከልነቷን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በራስ ዐቅም በማሳካት እንደገና ማስቀጠሏን አመልክተዋል፡፡…
“በኮሙኒኬሽን ተቋማትና የሕዝብ ግንኙነት መዋቅሮች የሚከናወኑ የተግባቦት ሥራዎች ዓላማ ተኮር እና ብሔራዊ ጥቅሞችን የሚያስገነዝቡ መሆን ይገባቸዋል” – የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
**************************** የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሀገራዊ የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡ በበይነ መረብ በተካሄደዉ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ የክልል እና ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ተቋማት እና የፌዴራል ተቋማት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ የአገልግሎቱ፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ተቋማት እና የፌዴራል ተቋማት የሕዝብ ግንኙነት የሥራ ክፍሎች የሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሞች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡…
የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየሠራን የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤን ለማስተናገድ ተዘጋጅተናል!
ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በጀመረቻቸዉ ጥረቶች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል፤ ለላቀ ስኬትም ጥረቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ በዚህ ወሳኝ ወቅት ኢትዮጵያ ከጣልያን መንግሥት እና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በመቀናጀት 2ኛዉን የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡ ይህም በኹለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ውስጥ ኢትዮጵያ እየተጫወተች ያለዉን ሚና የሚጎላ፣ በሥርዐተ ምግብ ዙሪያ የጀመረቻቸዉን ስኬታማ ተግባራት የሚያበረታታ ነው፡፡ ከዐራት ዓመታት…
“አሁን የተመዘገበው የኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ ዕድገት ሀገሪቱ ግብርና መር ኢኮኖሚ ስትከተል ከነበረችብት ጊዜ እንኳን በብዙ መልኩ የላቀ ነው፡፡”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶር)
ባሳለፈነው በጀት ዓመት የግብርና ዘርፍ 7 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት ያሰመዘገበ ሲሆን ከአጠቃላይ ዕድገታችን ዉስጥ ግብርና 2 ነጥብ 3 ድርሻ አለዉ፡፡ ከግብርና ምርት አንጻር ከሪፎርሙ በፊት በ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሩዝ ምርት 1.5 ሚሊዮን ኩንታል ሲሆን ባለፈዉ ዓመት ግን 63 ሚሊዮን ኩንታል ሩዝ ማምረት ተችሏል። ይህ የሩዝ ምርት በኢኮኖሚዉ እድገት ዉስጥ ትልቅ ለዉጥ መኖሩን የሚያሳይ ነዉ፡፡…
