ሀሳብ የለውጥ ኃይል ነው ምሁራን ደግሞ የለውጥ ወኪሎች ናቸው።”-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምሁራን በማህበረሰብ ውስጥ የሚፈጥሩት ለውጥ ሀገርን ወደ ብልጽግና እንደሚያሸጋግር በመጥቀስ ምሁራን የለውጥ ወኪልና የሀሳብ ኃይል መሆን እንደሚገባቸው አሳሰቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተበትን 75ኛ ዓመት በማስመልከት በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው። በመድረኩ ላይ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ምሁራን በሁለንተናዊ ሀገራዊ ጉዳዮች…
