የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ንረትን ለመቀነስ መንግሥት ምን አደረገ ?

“የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በአንዳንድ ሀገራት ከ400 ፐርሰንት በላይ የደረሰ የዋጋ ንረት እየተመዘገበ ነው፡፡ ከአፍሪካም 172 ፐርሰንት የደረሰ የዋጋ ንረት ያጋጠመ ሲሆን በጎረቤት ሀገራት እንኳን 72 ፐርሰንት የደረሰ የዋጋ ግሽበት ተመዝግቧል ። ከለውጡ ወዲህ መንግሥት አለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ቀድሞ በመገምገም ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ውድነት ጫናን በዘላቂነት ለመቀነስ በርካታ ኢንሼቲቮችን ቀርጾ…

“የገጠር ሽግግርን ለማረጋገጥ አንዱ መንገድ የእርሻ ማሽነሪዎችን ማበራከት ነው ።”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

በግብርናው ዘርፍ ያሉ አቅሞችና ጸጋዎችን ለይቶ በማልማት የአርሶደሩን ህይወት የሚቀይር መዋቅራዊ ሽግግር እየተደረገ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“ዛሬ በምስራቅ ሸዋ ዞን የነበረን ጉብኝት በክረምት የስንዴ ምርት ሥራዎች የተገኘውን ውጤት የምርት አሰባሰቡን በመመልከት ለመገምገም እና የበጋ ስንዴ ሥራ ማስጀመር ላይ ያተኮረ ነበር። በዚያው አካባቢ የሙዝ፣ ፓፓያ እና አሳ ክለስተር ሥራዎችንም ተመልክተናል። ነባሩ ባሕላዊ የግብርና ዘዴ አሁንም ያለ ቢሆንም በሰፊው ለማረስ የሚያስችለው ሜካናይዜሽን እያደገ በመሄዱ የአካባቢውን የግብርና ብቁነት እና ምርታማነት እያሳደገ ይገኛል። ወደኋላ መለስ…

የፖለቲካ ሥልጣንን በተመለከተ

“ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቸኛው መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነው፡፡ ችግሮች አሉኝ የሚሉ አካላት ጋር ቁጭ ብሎ በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም በራችን ክፍት ነው። የኢትዮጵያን እድገት የማይሹ ሀገራት በጦርነት እንደማያሸንፉን ያውቁታል፡፡ ያላቸው ምርጫ ባንዳዎችን መላክ ነው። ኢትዮጵያን በቅጡ ያላወቁ የውስጥ ባንዳዎች ደግሞ ከጠላት ጋር በማበር ዓላማቸውን የሚያሳኩ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ፈጽሞ ሊሳካ አይችልም። “ ጠቅላይ…

“አሁን የተመዘገበው የኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ ዕድገት ሀገሪቱ ግብርና መር ኢኮኖሚ ስትከተል ከነበረችብት ጊዜ እንኳን በብዙ መልኩ የላቀ ነው፡፡”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶር)

ባሳለፈነው በጀት ዓመት የግብርና ዘርፍ 7 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት ያሰመዘገበ ሲሆን ከአጠቃላይ ዕድገታችን ዉስጥ ግብርና 2 ነጥብ 3 ድርሻ አለዉ፡፡ ከግብርና ምርት አንጻር ከሪፎርሙ በፊት በ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሩዝ ምርት 1.5 ሚሊዮን ኩንታል ሲሆን ባለፈዉ ዓመት ግን 63 ሚሊዮን ኩንታል ሩዝ ማምረት ተችሏል። ይህ የሩዝ ምርት በኢኮኖሚዉ እድገት ዉስጥ ትልቅ ለዉጥ መኖሩን የሚያሳይ ነዉ፡፡…