“ኢትዮጵያ ታሪኳን በራሷ ልጆች እየጻፈች መሆኑን የ100 ቀናት ሪፖርት ማሳያ ነዉ” ወ/ሮ እናትአለም መለሰ
የዓለም መሪዎች በ100 ቀናት የሰሩት ስራዎች ላይ ዜናዎች እንደሚወጣ ያነሱት የመንግሥት ኮሙኒኬሺን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትአለም መለስ በአፍሪካ ግን ይህ አሰራር ያልተለመደ መሆኑን አንስተዋል፡፡ የአፍሪካ መሪዎች አያልሙም ካለሙም አይተገብሩም የሚል ትቺት እንዳለም ግልፀዋል፡፡ ከለውጡ ወዲህ በኢትዮጵያ በ100 ቀናት ዉስጥ የሚነገር ታሪክ ነጥሎ ያየ፤ ሃሳቡን መሬት የሚያወርድ፤ አካሄዱን ደግሞ በትክክል ከህዝብ ተጠቃሚነት ጋር ማቆራኘት የሚችል አመራር…
