ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ያላት ብዝኃነት ልዩ ዐቅም የሚፈጥርላት መሆኑ ተገለፀ።

“ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ መልእክት የኅብር ቀን በመላዉ ኢትዮጵያ እየተከበረ ነው፡፡ ብዝኃነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል፣ ብዝኃነት ለኢትዮጵያ ያበረከተዉን ፋይዳ እና በቀጣይም በላቀ ደረጃ እንዴት መጠቀም እንደሚገባ የሚያስገነዘብ የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ጥንታዊና ገናና ታሪክ…

“ብዝኃነት ዐቅም፣ ውበት እና ጌጥ ነው፡፡” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

“ብዝኃነት ዐቅም፣ ውበት እና ጌጥ ነው፤ በዚያዉ ልክ ልንጠቀምበት ይገባል” ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ አስገነዘቡ፡፡ “ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ መልእክት የኅብር ቀን በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተከብሯል፡፡ በመድረኩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ብዝኃነት የተሰናሰነ ዐቅም መኾኑን በመረዳት የማንነት፣ የሐሳብ፣ የታሪክ፣ የባህል እና የመሳሰሉትን ብዝኃነቶች የሚያስተናግድ ሥርዐት እየዳበረ እንደሚገኝ…

ፈታናዎችን በመገንዘብና የመሻገሪያ መንገዶችን ለመተለም ዜጎች ምንጊዜም ንቁ መሆን አለባቸዉ- ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

በመጪዉ ዓመት የሚኖሩ ፈታናዎችን አስቀድሞ በመገንዘብና የመሻገሪያ መንገዶችን ለመተለም ዜጎች ምንጊዜም ንቁ መሆን አለባቸዉ ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ የዘንድሮ የጷጉሜን ቀናት ስያሜን ተንተርሶ በሀገራዊ ጉዳዮች  ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም የተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት ሀገሪቱ ዉስብስብ ችግሮችን በመሻገር በሁሉም ዘርፎች አኩሪና እምርታዊ ድሎች ያስመዘገበችበት ዓመት እንደ ነበር አስታዉሰዋል፡፡…

የተዋሐደች እና የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት በአፍሪካ ሕዝቦች መካከል ድልድይ መገንባትና ትስስር ማጠናከር ላይ መሥራት አለባቸው፡- ዶ.ር ለገሠ ቱሉ

ቀን-21-12-2017 የአፍሪካ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የኅብረቱ አጀንዳ 2063 እንዲሳካ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ባህል ትስስር መጠናከር ላይ እንዲያተኩር የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ.ር) አሳሰቡ፡፡ 15ኛዉ የምሥራቅ አፍሪካ የኮሙኒኬሽን ማኅበር (East African Communication Association) ኮንፈረንስ አዲስ አበባ ላይ እየተካሄደ ነው፡፡ በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ.ር)…

የፕሬስ መግለጫ

ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ማሳያ ናቸው። ብዝኃነት እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገለጫዋ የኾነችው ኢትዮጵያ የክረምቱን መገባደድ የሚያበስሩ ትውፊቶች ባለቤት ናት። ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ልጃገረዶች ወደ ዐደባባይ በመውጣት የሚያሰሟቸዉ ኅብረ ዝማሬዎች በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የክረምቱን መገባደድ፤ በየጋራ ሸንተረሩ የአበቦችን መፍካት፣ የምንጮችን መጥራት እና የቡቃያዎችን ማፍራት ያበስራሉ። ከእነዚህ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች መካከል ከነሐሴ…

በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ የሚነቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭን እየተቀበሉ ነዉ!

መንግስት በተለያዩ ሀገሪቱ አካባቢዎች ተንቀሳቅሰዉ የህዝቡን ሰላም የሚያዉኩ አካላትን ለመቆጣጠር የሰላም አማራጮችን ሲከተል ቆይቷል፡፡በዚህም በርካታ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበልና የታህድሶ ስልጠና በመዉሰድ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡ ሰሞኑን በኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ ዞን እና በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተሳሳተ ዓላማ ወደ ጫካ ገብተው የነበሩ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ ተቀብለው ገብተዋል። በበርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች…

የሚዲያ ኢንዱስትሪዉ ወደ ዲጂታል እንዲሸጋገር ድጋፍ እየተደረገ ነዉ

የሚዲያ እንዱስትሪዉ በሂደት ወደ ድጂታል እንዲሸጋገር በመንግስት ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በራሱ አቅም ያበለጸገውን የሞባይል መተግበሪያ (አፕ) በዛሬው ዕለት በይፋ አስመርቋል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የኢቢሲ የሞባይል መተግበሪያ ማስጀመሪያ ዝግጀት ላይ ተግኝተዉ ባስተላለፉት መልዕክት፣ መንግስት የሚዲያ እንዱስትሪዉን ዐጠቃላይ ወደ የዲጂታል ሽግግር…

ተለዋዋጭ ነባራዊ ኹኔታዎችንና ሀገራዊ አቅጣጫዎችን ታሳቢ ያደረገ የሚዲያ እና ኩሙኒኬሽን ሥራ በበጀት ዓመቱ ትኩረት ይሰጠዋል፦ ዶ.ር ለገሠ ቱሉ

ተለዋዋጭ ነባራዊ ኹኔታዎችንና ሀገራዊ አቅጣጫዎችን ታሳቢ ያደረገ የሚዲያ እና ኩሙኒኬሽን ሥራ በበጀት ዓመቱ ትኩረት እንደሚሰጠዉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ.ር) ገለጹ። የአገልግሎቱ የ2018 በጀት ዓመት የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዕቅድ ላይ ውይይቶች ተደርገዋል። በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ አቅጣጫ ያስቀመጡት ዶ.ር ለገሠ ” ነባራዊ ኹኔታዎችን መሠረት አድርጎ የኢትዮጵያን ማንሠራራት ማጽናት ላይ ያተኮረ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሥራ…

እንደ ሀገር ለተመዘገቡ የልማትና ዲሞክራሲ ግንባታ ስኬቶች፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና ከፍተኛ ነው – ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

(ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም) በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት እንደ ሀገር የተመዘገቡ በርካታ የልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ ስኬቶች፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዕቅድን በአዳማ ከተማ እየገመገሙ ነው። የተቋሙ የዘንድሮ አፈጻጸም ከባለፈዉ ዓመት ጋር ሲነጻጸር ዉጤታማ የኮሙኒኬሽን ሥራዎች…

አረንጓዴ አሻራ ለኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ ነዉ _ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

(ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም) አረንጓዴ አሻራ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና አጠቃላይ ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 700 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር ዘነበወርቅ የሚገኘዉ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግቢ አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጧል፡፡ በኢቢሲ ግቢ በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በርካታ የቡና ችግኞች ተተክለዋል፡፡…