የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በሚኒስትር መስሪያቤታቸው የተመዘገቡ ዐበይት ስኬቶችን አቅርበዋል።
በዚህም ዘርፉ ከለውጡ በፊት ሲቸገርበት የነበሩ መጠነ ሰፊ ክፍተቶችን በመለየት ፈጣን መፍትሔ በመስጠት ሰፊ ስኬቶችን አስመዝግቧል።ከተገኙ ስኬቶች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የዜጎችን መብት ጥበቃ፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ። አደረጃጀቶችን በመደገፍና በማጠናከር መብትና ግዴታ በማወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ የአቅመ ደካማ ዜጎችን የመደገፍና የማገዝ ባህል ማሳደግ ጥቂቶቹ ናቸው።እነዚህ ስኬቶች ቁጥር ብቻ ሳይሆኑ በተጨባጭ 4,330,948 የሚሆኑ…
