“ኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ሽግግርን እዉን ለማድረግ ስኬታማ ስራዎችን አከናዉናለች” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለዉ 2ኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ (UNFSS+4) ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ሽግግርን እዉን ለማድረግ ስኬታማ ስራዎችን ስታከናዉን መቆየቷን ገልጸዋል፡፡ በመላው አፍሪካ የምግብ ሥርዓትን ለመለወጥ እየተሰሩ ያሉ አኩሪ ስራዎችንም አድንቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዓለም አቀፍ መሪዎች፣ የልማት አጋሮች እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተገኙበት ባደረጉት ንግግር፣ ረሃብን፣…
