የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 46ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
በዚህም መሰረት: 1. የመካከለኛ ዘመን 2018-2022 የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ ማዕቀፉ የመንግስትን ገቢ መሠረት በማስፋት ወጪ ለመሸፈንና የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ፣ ከመንግስት ገቢ አሰባሰብ እና ሀብት አመዳደብ አኳያ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በማመላከት ለቀጣይ በጀት አመት የበጀት ዝግጅት መነሻ ሆኖ እንዲያገለግል ማዕቀፉ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በማዕቀፉ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ…
