53ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 53ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ 1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው መደመር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው በአዋጅ ቁጥር 1294/2015 መሠረት ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ የሚቋቋም ሲሆን በዘርፉ ወጣቶችን ለማሰልጠንና ለሀገር ግንባታ ወሳኝ የሆኑ ምሁራንን…

