የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትናንትናው እለት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ በመደበኛ የሕግ ማስከበር ስርአት መቆጣጠር እንደማይቻል በመግለጽ ለፌዴራል መንግስት ጥያቄ ማቅረቡን አስታውሰዋል፡፡ ይህን ተከትሎ መንግሥት ሰላምን፣ የሃገር ደህንነትን እንዲሁም ሕገ መንግስታዊ ስርአትን የማስከበር ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ በክልሉ የሚታየውን ሕገ ወጥ…
