የመሶብ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎት
ዛሬ ስራ የጀመረው፣ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማህበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው። ለአገልግሎት የተደራጀው አውቶቡስ ሙሉ ቁሳቁስ የተሟላለትና ራሱን የቻለ የአገልግሎት ማዕከል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ቀልጣፋና አስተማማኝ አሰራርን ለማረጋገጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ስርዓቶችን አቀናጅቶ የያዘ ነው። አውቶቡሱ የአገልግሎት ፍሰቱን የሚያደራጅ የሰልፍ ማስተናገጃ ስርዓት ያለው ሲሆን፣ የተለያዩ የክፍያ አማራጮችንም አካቷል። ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን ኃይል በከፊል…
