ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዳር እና ታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም ቁልፍ የሆኑ ተከታታይ ሀገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተግባራትን አከናውነዋል።
ሁሉም ክንውኖች የኢትዮጵያን ተፈላጊነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በጽኖ መሠረት ላይ ያስቀመጡ ናቸው። የህንድ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን ተከትሎ፥ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያካሄዱት የሁለትዮሽ ውይይት እና በሀገራቱ መካከል የተደረሰው ሁሉን አቀፍ ስምምነት ትልቅ ትርጉም ተሰጥቶታል። የመሪዎቹ ውይይት በዋናነት በንግድ እና ኢንቬስትመንት፣ በዲጂታይዜሽን እና ቱሪዝም ያለውን ትብብር በኢትዮጵያ እና…
