ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ረቡዕ እለት በሀላባ እና ከምባታ ዞኖች የሞዴል የገጠር መንደሮችን ማስረከባቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ደግሞ በሀዲያ እና ስልጤ ዞኖች የተገነቡትን አስረክበዋል።
ረቡዕ በሀላባ እና ከምባታ ዞኖች የነበረንን የሞዴል የገጠር መንደሮች ርክክብ ሥነሥርዓት በመቀጠል ዛሬ ደግሞ በሀዲያ እና ስልጤ ዞኖች የተገነቡትን አስረክበናል። እነኚህ ባለሶስት መኝታ ቤት መኖሪያዎች ለማብሰል የሚያገለግል የባዮጋዝ መሣሪያ፣ የፀኃይ ኃይል ማመንጫ፣ የዶሮ ማርቢያ፣ የተለየ የእንስሳት በረት የተሟላላቸው ሲሆን በተመጣጣኝ አነስተኛ ወጪ ከአካባቢ በሚገኙ ግብዓቶች የተሻለ መኖሪያ ከማስገኘት አንፃር ለገጠሩ ማኅበረሰብ ብልጽግና ያለንን ሕልም የሚያሳይ…

