የብሔር፣ ብሔረ-ሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሕገ መንግሥታዊ ቃል ኪዳናችንን የምናድስበትና የብዝኃነታችንን ዐቅም የምናልቅበት ቀን ነው!
ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ የሚገለጽ ብዝኃነት ባለቤት ናት፡፡ የቋንቋ፣ የባህል፣ የብሔር፣ የሃይማኖት፣ የፖለቲካዊ አመለካከት፣ የዕድሜ፣ የፆታ ወ.ዘ.ተ ብዝኃነቶቿ የሚያስጌጧት ድንቅና ቀደምት ሀገር ናት፤ ኢትዮጵያ፡፡ ይህንን ብዝኃነቷን እንደ እሴት የምታዳብርበት፣ እሴቱን ወደ መፈጸም ዐቅም የምትለውጥበት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐት ባለቤትም ናት፡፡ ለዚህም ነው የጋራ የቃል ኪዳን ሰነድ በሆነው ሕገ መንግሥታችን አንድ የጋራ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመገንባት በነፃ…
ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች ዕምርታዊ ዉጤቶችን እያስመዘገቡ ነዉ
ህዳር 5/2018 ዓ.ም እንደ ሀገር ሁሉንም አከባቢዎች ከተስፋ ወደ ሚጨበጥ ብርሃን ለማሸጋገር እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች እምርታዊ ዉጤቶችን እያስገኙ እና የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ ይገኛል፡፡ “ዲሞክራሲያዊ አንድነት፣ ለህብረብሔራዊ መግባባት” በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚከበረውን 20ኛዉ የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓልን በማስመለከት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የፌድሬሽን ም/ቤት እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጋራ በመሆን የክልሉን…
በአንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ.ዴሌቦ ህልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለፁ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሰተላለፉት የሀዘን መግለጫ “አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ላዺሶ ጌ. ዴሌቦ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ማለፋቸውን በታላቅ ኀዘን ሰማሁ። ነፍሳቸውን በዐጸደ ገነት እንዲያኖርልን እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንዲሰጥልን እመኛለሁ።” ብለዋል፡፡
ስኬቶቻችን የሰንደቃችን ከፍታ የሚጨምሩ ናቸው
********************************** ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት እመርታዊ ስኬቶችን እያስመዘገበች የሚመጥናትን ከፍታ እየያዘች ትገኛለች። ለዘመናት የቁጭት እና እንጉርጉሮ ትርክት ምንጭ የነበረዉን ዓባይን ገርታ የኃይል እና ብርሃን ምንጭ አድርጋለች፡፡ በንጋት ኃይቅ በምግብ ሉዓላዊነቷ ላይ ጉልህ ሚና የሚጫወት የዓሣ ምርት ማግኘት ችላለች፤ ዐዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ደሴቶችንና ከተሞችን ፈጥራለች፡፡ የዓባይን የቁጭት ትርክት ወደ ድል እና አሸናፊነት ብስራት ቀይራለች፡፡ ተጨማሪ…
በእናንተ ገንዘብ ሀገር እየተሰራች መሆኑን ዳግም በኩራት ልገልጽላችሁ እወዳለሁ።
https://web.facebook.com/share/v/19pueTyA2h
ኢሬቻ ኢትዮጵያ ለዓለም የምታበረክተዉ ድንቅ እሴቷ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ለዓለም አበርክታለች፡፡ እሴታቸዉን ጠብቀዉ ለዘመናት በሕዝብ እየተከበሩ የዘለቁ ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላትንና ትውፊቶቻቸዉን በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ፣ የትምህርት እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የሰው ልጆች ሁሉ ሀብት ተብለው እንዲመዘገቡም አድርጋለች፡፡ ለምዝገባ በሂደት ላይ የሚገኙ በርካታ እሴቶች ባለቤትም ነች፡፡ ኢሬቻ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ በየዓመቱ የሚከበር የይቅርታ እና የምስጋና በዓል ነው፡፡…
ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ነገዋን እየሠራች ነው!
ኢትዮጵያ ነገዋን ዛሬ ላይ ለመሥራት እያደረገች ያለውን ጥረት እና የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስተዋወቅ 5ኛዉን የጳጉሜን ቀን “የነገዉ ቀን” በሚል ስያሜ እና “ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” በሚል መሪ መልእክት እያከበረች ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከራሷ ባሻገር የአፍሪካን ማንሰራራት ለማብሰር ዛሬ ላይ ነገዋን እየሠራች ነው፡፡ ለአምስተኛዉ የኢንዱስትሪ አቢዮት የሚመጥን ትውልድ መቅረጽን፣ ለኢንዱስትሪ ዕድገቱ የሚመጥን ታዳሻ ኃይል ማቅረብን፣ የዘመኑ ከተሞችን መፍጠርን፣…
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
******************* እንኳን ጳጉሜን 3 የእመርታ ቀን አደረሳችሁ! የእመርታ ቀንን የምናከብረዉ የጀመርነዉን የከፍታ ጉዞ በማላቅ እና በማጽናት የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት በበርካታ እመርታዊ ለውጦችን አስመዝግባለች፡፡ ወደተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ውስጥ ገብታ ያለመችዉን አሳክታለች፡፡ የተረጋጋ ማክሮ–ኢኮኖሚ መፍጠር፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ፣ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ተወዳዳሪነትና የገበያ ድርሻ ማሳደግ፣ የማዕድን ዘርፉን ዐቅም እና ሕጋዊ ሥርዐት…

