ከአራት ኪሎ-ቀበና-ኬንያ ኤምባሲ ኮሪደር ልማት ሥራ ተጠናቋል።











የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በእስካሁኑ ለተቋሙ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የምስጋና እና የሽኝት መረሃ ግብር አድርጓል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ በመረሃግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተቋሙ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ለሀገሪቱ ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ትልቅ አሻራ ማስቀመጣቸዉን ገልጸዋል፡፡ አገልግሎቱ በ2014 ዓ.ም እንደ አዲስ ሲመሰረት ከምንም በመነሳት…
መንግስት የኢትዮጵያን የወርቅ ክምችት ለማሳደግ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካዎችን ማስፋፋት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡ ዛሬ ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉጂ ወርቅ የማምረት ስራ ላይ የተሰማራዉን የሚድሮክ ጎልድ ኩባንያ የስራእንቅስቃሴን ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ኩባንያዉ በዘርፉ ቀዳሚ በመሆኑ ለኢትዮጵያ የማዕድን አከባቢ ትልቅ አስተዋጽዖ ማበርከቱን ገልፀዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ የወርቅ ሀብትን በሚገባ በማልማትና…
ሰላማዊ ካሳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሕብረ ብሄራዊነት የተከበረባት ጠንካራ አንድነት ያላት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ታላቁን ገዥ ትርክት በጋራ ልንገነባ ይገባል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊ ካሳ ተናገሩ፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ዛሬ በጀመሩት ውይይት ሚኒስትር ዴኤታዋ እንዳሉት እንደ መንግስት ኮሙኒኬሽን አመራርና ባለሙያ ለሃገራዊ ግንባታ አዎንታዊ ገዥ…
“ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ መልእክት የኅብር ቀን በመላዉ ኢትዮጵያ እየተከበረ ነው፡፡ ብዝኃነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል፣ ብዝኃነት ለኢትዮጵያ ያበረከተዉን ፋይዳ እና በቀጣይም በላቀ ደረጃ እንዴት መጠቀም እንደሚገባ የሚያስገነዘብ የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ጥንታዊና ገናና ታሪክ…
ከክረምቱ ዝናብ ጋር ተያይዞ በአንድ አንድ የሃገራችን አካባቢዎች በደረሱ የመሬት መንሸራተትና የዉሃ ሙሌት ምክንያት የበርካታ ዜጎቻችን ሕይወት አልፏል፤ የአካል ጉዳትና የንብረት መውደም አደጋም ደርሷል፡፡በትናንትናው ምሽት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ ግሽሬ ጉዱ ሞና ሆሞ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 (ስድስት) ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ የአካል…
የ2018 ሀገራዊ የልማት አቅድ በሁሉም ዘርፎች የተገኙ እምርታዊ ዉጤቶችን የሚያስቀጥልና ለላቀ ዉጤት የተደመረ አቅም የሚፈጥር እቅድ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የአገልግሎቱ አመራርና ሰራተኞችም በእቅዱ ላይ ዛሬ ዉይይት አድርገዋል፡፡ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ሀገራዊ እቅዱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም በሁሉም ዘርፎች ያስመዘገበችዉ የኢኮኖሚ እድገት እምርታ የታየበት መሆኑን…