የፕሪቶሪያ ስምምነት መነሻና መድረሻው ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ተቋማትን ማክበር ነው!






የፕሪቶርያው ስምምነት ከምንም በላይ ተግባራዊ ምላሽ ይፈልጋል ሕወሐት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት እንዲከበር መጠየቁን የፌዴራል መንግሥት በአንክሮ ተመልክቶታል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ዋነኛው መፍትሔ የፕሪቶርያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን የኢፌድሪ መንግሥት በጽኑ ያምናል። ይሄንንም በተመለከተ የፌዴራሉ መንግሥት ከመነሻው እስካሁን ያለው አቋም ወጥ እና የማይናወጥ ነው፡፡የመግለጫውን ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያገኛሉ…
********************************** ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት እመርታዊ ስኬቶችን እያስመዘገበች የሚመጥናትን ከፍታ እየያዘች ትገኛለች። ለዘመናት የቁጭት እና እንጉርጉሮ ትርክት ምንጭ የነበረዉን ዓባይን ገርታ የኃይል እና ብርሃን ምንጭ አድርጋለች፡፡ በንጋት ኃይቅ በምግብ ሉዓላዊነቷ ላይ ጉልህ ሚና የሚጫወት የዓሣ ምርት ማግኘት ችላለች፤ ዐዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ደሴቶችንና ከተሞችን ፈጥራለች፡፡ የዓባይን የቁጭት ትርክት ወደ ድል እና አሸናፊነት ብስራት ቀይራለች፡፡ ተጨማሪ…
ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ ብዝኃ ማንነት ደምቃ፣ ፀንታና ታፍራ የኖረች፣ ብዝኃ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት የሆነች ድንቅ ሀገር ናት፡፡ ብዝኃነታችን የጥንካሬያችን፣ የሥልጣኔያችን፣ የአይበገሬነታችን፣ የክብራችን፣ የነፃነታችን እና የአልሸነፍ ባይነታችን ምሥጢር ነው፡፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙ ጥንታዊ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ቦታዎች እና የኪነ ሕንጻ ሀብቶቻችን የብዝኃነታችን ውጤቶች ናቸው፡፡ የአክሱም ሐውልቶች፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የለጋ ኦዳ ዋሻ…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባለፉት ሳምንታት ከመላዉ ኢትዮጵያ ከተውጣጡ ከንግዱ ማኅበረሰብ፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ከመምህራን ተወካዮች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃን ተወካዮች ጋር ሁሉን አቀፍ እና ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል። ውይይቶቹ በየዘርፉ ያሉ ፍላጎቶችንና ተግዳሮቶችን ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ፊት ለፊት ለማቅረብ እድል የፈጠሩ፣ ከዚህም አኳያ በአጭር ጊዜ ሊፈቱ የሚችሉ ጉዳዮች አቅጣጫ የተሰጠባቸው እና…
ኢትዮጵያ ነገዋን ዛሬ ላይ ለመሥራት እያደረገች ያለውን ጥረት እና የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስተዋወቅ 5ኛዉን የጳጉሜን ቀን “የነገዉ ቀን” በሚል ስያሜ እና “ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” በሚል መሪ መልእክት እያከበረች ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከራሷ ባሻገር የአፍሪካን ማንሰራራት ለማብሰር ዛሬ ላይ ነገዋን እየሠራች ነው፡፡ ለአምስተኛዉ የኢንዱስትሪ አቢዮት የሚመጥን ትውልድ መቅረጽን፣ ለኢንዱስትሪ ዕድገቱ የሚመጥን ታዳሻ ኃይል ማቅረብን፣ የዘመኑ ከተሞችን መፍጠርን፣…