ኢትዮጵያ እየተከለች ነዉ።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ (ዶ.ር) በአንድ ጀንበር #600_ሚሊየን_ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ላይ አሻራቸዉን አሳረፉ።


ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት 250ሺህ ቶን የማር ምርት ማግኘቷን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመላከተ፡፡ በግብርናዉ ዘርፍ በተለይም የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ተቀርጾ እየተተገበረ ያለዉ ሀገራዊ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ከፍተኛ ዉጤት ማስመዝገቡን ቀጥሏል፡፡ በምግብ ራስን ለመቻል መንግስት በሌማት ትሩፋት እና በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየከናወነ ያለው የግብርና እና የአከባቢ ጥበቃ ልማት…
የ2018 ሀገራዊ የልማት አቅድ በሁሉም ዘርፎች የተገኙ እምርታዊ ዉጤቶችን የሚያስቀጥልና ለላቀ ዉጤት የተደመረ አቅም የሚፈጥር እቅድ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የአገልግሎቱ አመራርና ሰራተኞችም በእቅዱ ላይ ዛሬ ዉይይት አድርገዋል፡፡ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ሀገራዊ እቅዱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም በሁሉም ዘርፎች ያስመዘገበችዉ የኢኮኖሚ እድገት እምርታ የታየበት መሆኑን…
“ዓላማ ተኮር ተግባቦት ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ መልእክት የፌዴራል ተቋማት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን የሥራ ኃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ውይይት ተካሂዷል፡፡ በአፍሪካ የአመራር ልሕቀት አካዳሚ ዛሬ የተካሄደዉ የውይይት መድረክ ላይ የዘርፉን አጠቃላይ አቅጣጫ ያመላከቱት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ.ር) ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት በተመዘገቡ ኹለንተናዊ ስኬቶች የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ጉልህ ሚና መጫወቱን አውስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ…
“የምትተክል ሃገር የሚያጸና ትውልድ” የ600 ሚሊዮን ችግኞች የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከማለዳው12 ሰአት ጀምሮ እስከ አመሻሽ 12 ሰዓት በመላ ሃገሪቱ ሲካሄድ ለኢትዮጵያዊያንና ለመላው ዓለም መረጃውን ለማድረስ በከፍተኛ ትጋት ኃላፊነታችሁን ለተወጣችሁ የመገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላቅ ያለ ምሥጋናውን ያቀርባል፡፡ ሰላማዊት ካሳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ በዚህ ለአንድ ቀን በተካሄደው የአንድ…
መንግስት ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ምላሹም እንደሚከተለው ይቀርባል፡- ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ድርጅት እ.ኤ.አ. ጁን 1 ቀን 2023 (ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም) በሀገራችን በአንዳንድ አካባቢዎች ጉልህ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚገልጽ መሰረተ ቢስ ሪፖርት አውጥቷል ብሏል። በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ግጭት በርካታ አካባቢዎችን ለጉዳት ያጋለጠ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ የተወሰነ…
የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ቴክኖሎጂን ለኢትዮጵያ ሁሉ አቀፍ ልማት በማዋል ረገድ የላቀ ትብብር እና የፈጠራ ስራዎች ወሳኝ ሚና ያላቸዉ መሆኑን ገለጹ፡፡ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ዛሬ ግንቦት 8/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል የተጀመረዉን የምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የቴክኖሎጂ ኤክሲፖ (ኢቴክስ ኤክስፖ 2025) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋትና ለሀገሪቱ ልማት ላይ…