በተባበረ ክንድ የኢትዮጵን ብልፅግና እዉን እናደርጋለን፡፡ ‘

ምክር ቤቱ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች፡- 1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ነው፡፡ ኮሚሽኑ ሀገራችን የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ መንገድ ከዓለም አቀፍ ማዕቀፎች ጋር በተጣጣመ መልኩ በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በምግብ ዋስትና፣ በጤና አገልግሎት፣ በሳይንስ እና ምርምር ዘርፎች ላይ ለመጠቀም የምታደርገውን ጥረት የመምራትና…
ባሳለፈነው በጀት ዓመት የግብርና ዘርፍ 7 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት ያሰመዘገበ ሲሆን ከአጠቃላይ ዕድገታችን ዉስጥ ግብርና 2 ነጥብ 3 ድርሻ አለዉ፡፡ ከግብርና ምርት አንጻር ከሪፎርሙ በፊት በ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሩዝ ምርት 1.5 ሚሊዮን ኩንታል ሲሆን ባለፈዉ ዓመት ግን 63 ሚሊዮን ኩንታል ሩዝ ማምረት ተችሏል። ይህ የሩዝ ምርት በኢኮኖሚዉ እድገት ዉስጥ ትልቅ ለዉጥ መኖሩን የሚያሳይ ነዉ፡፡…
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና በህዝቡ ትብብር እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በእጅጉ ሊያሳድጉ የሚችሉ መሆናቸው ተገለጸ፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ያዘጋጁት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ቡድን ጉብኝት በሁለተኛ ቀን ቆይታው በድሬዳዋ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል። በዛሬው እለት የድሬዳዋ የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ፣ የድሬዳዋ ስታዲየም ማሻሻያ ፕሮጀክት፣ የድሬዳዋ…
መንግስት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዪ መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት እና ተደራሽ የማድረግ ስራዎችን በተገባደደዉ የበጀት አመት ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል።በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ2016 የበጀት ዓመት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 20,664 ፕሮጀክቶች ለምረቃ ተዘጋጅተዋል። ፕሮጀክቶቹ በክልል፣ በዞን እና በወረዳ ደረጃ በሁለት ዙር የሚመረቁ ይሆናል።እነዚህ ፕሮጀክቶች በዋናነት የህብረተሰቡን የዘመናት የመልማት…
በሕዝብ ግፊትና በፓርቲ ሳቢነት የመጣው ሀገራዊ ለውጥ፣ የመጀመሪያውን ምእራፍ እየተሻገረ ነው፡፡ በዚህ የመጀመሪያ ምእራፍ የለውጡን ሐሳቦች በቃልና በተግባር ተገልጠዋል፡፡ የለውጡ ፈተናዎችም አካል ገዝተው በሚገባ በመገለጣቸው ሕዝብ ዐውቆ እንዲታገላቸው ተደርጓል፡፡ ይሄም የለውጡን ፍሬዎች ለማጎምራት፣ የለውጡን ፈተናዎችንም ለመርታት ዕድል ሰጥቷል፡፡ ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ሲጠየቁ የነበሩ ጥያቄዎች ከቃል አልፈው ተግባራዊ ምላሽ አግኝተዋል፡፡ የፖሊሲ፣ የሕግ…