Similar Posts

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የክልል የኮሙኒኬሽን ተቋማት ያሉበትን ደረጃ ለማወቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ በዘጠኝ ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ሲያካሂድ የቆየውን የክትትልና ድጋፍ ሥራ አጠናቋል
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የክልል የኮሙኒኬሽን ተቋማት ያሉበትን ደረጃ ለማወቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ በዘጠኝ ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ሲያካሂድ የቆየውን የክትትልና ድጋፍ ሥራ አጠናቋል፡፡ አገልግሎቱ ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል የተቀናጀ እና የተናበበ የተግባቦት ሥራ ከፌዴራል እና ከክልል ኮሙኒኬሽን ተቋማት ጋር መዘርጋት፣ በትብብር መሥራት እና ለክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮዎች የተግባቦት ሥራን ለማከናወን የሚያስችል አቅም መገንባት ይገኝበታል፡፡ ይህንን ኃላፊነቱን…

ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል።
የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ስድስት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን ልንተክል ኢትዮጵያውያን ሁሉ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል። ህፃናት ተስፋቸውን ተክለዋል። ወጣቶች ጽናተቸውን አሳይተዋል። አረጋውያን ውርስ አኑረዋል። ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከቤታቸው ወጥተው የማይደበዝዝ አሻራ አኑረዋል። በማበራችን እና በመጽናታችን በአለም በሌላ ስፍራ በአንድ ጀምበር ያልተደረገውን እኛ ኢትዮጵያውያን አድርገነዋል።…

ዳግም ግጭት እንዳይፈጠር የሃይማኖት አባቶች፣ ባለሀብቶች፣ ምሁራን እና ኤምባሲዎች የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ መንግሥት አሳሰበ፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ያስገኘዉ ሰላም ዘላቂነት እንዲኖረዉ እና የክልሉ ሕዝብ ሰላም፣ ልማት እና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲመለሱ ባለድርሻ አካላት ሚናቸዉን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በመገኘት ለምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ አንጻራዊ ሰላም መኖሩንና መጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ “በፕሪቶሪ የተደረሰዉ የሰላም…
የሚዲያ ኢንዱስትሪዉ ወደ ዲጂታል እንዲሸጋገር ድጋፍ እየተደረገ ነዉ
የሚዲያ እንዱስትሪዉ በሂደት ወደ ድጂታል እንዲሸጋገር በመንግስት ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በራሱ አቅም ያበለጸገውን የሞባይል መተግበሪያ (አፕ) በዛሬው ዕለት በይፋ አስመርቋል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የኢቢሲ የሞባይል መተግበሪያ ማስጀመሪያ ዝግጀት ላይ ተግኝተዉ ባስተላለፉት መልዕክት፣ መንግስት የሚዲያ እንዱስትሪዉን ዐጠቃላይ ወደ የዲጂታል ሽግግር…

የዜጎች እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተረጋገጠባትና የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶች የተስፋፉባትን ኢትዮጵያ ዕውን እናደርጋለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡ በውይይቱም በተሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝር ምክክር መደረጉን ገልፀዋል፡፡ የዜጎች እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተረጋገጠባትና የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶች የተስፋፉባትን ኢትዮጵያ ዕውን እናደርጋለን ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡ Post Views: 60

ወቅታዊ መረጃ
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን በማሰብ ከነገ ሐምሌ 20 ቀን ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት ብሄራዊ የሃዘን ቀን ሆኖ እንዲታወጅ ወስኗል። በእነዚህ ቀናት በሁሉም የሃገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች፣ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ…