25 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን 48 ቢሊዮን ዶላር ለሀገራቸው ኢንቨስት አድርገዋል !!
ባለፉት 6 አመታት ሕዝብን በማስተባበር በተሰራው የአርንጓዴ ዐሻራ መረሃ ግብር 25 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ተሳትፈው 48 ቢሊዮን ችግኞችን ተክለዋል፡፡
አንድ ችግኝ ከመጀመሪያው ዝግጅት ጀምሮ እስከመጨረሻ ድረስ 1 ዶላር ወጪ ቢፈጅ እንኳን ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸው 48 ቢሊዮን ዶላር ገዳማ ኢንቨስት አድርገዋል እንደማለት ነው ፡፡
ይህን ያህል ገንዘብ የሚያበድረን ሃገርም ሆነ የሚለግሰን ተቋም የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶር) የተገኘው ውጤት ኢትዮጵያዊያን ተባብርን ለሀገራችንና ለዓለም አየር ንብርት ለውጥ 48 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት አድረጋናል ለማለት ያስችላል ብለዋል፡፡

